Your cart is currently empty!
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመደበኛ እቃ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት
|
የሎት አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን (በኢትዮጵያ ብር)
|
1 |
ስቴሽነሪ እና ቶነሮች
|
ሎት1 |
30,000 ብር
|
2 |
የፅዳት እቃዎች
|
ሎት2 |
40,000 ብር
|
3 |
የደንብ ልብስ
|
ሎት3 |
20,000 ብር
|
4 |
የቢሮ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች
|
ሎት4 |
50,000 ብር
|
5 |
የመኪና አላቂና ቋሚ እቃዎች
|
ሎት5 |
20,000 ብር
|
6 |
የኤሌክትሪክና የቧንቧ ጥገና እቃዎች
|
ሎት6 |
10,000 ብር
|
7 |
የእንጨት ስራ ት/ከፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት7 |
50,000 ብር
|
8 |
የኤሌከትሪክሲቲ ት/ ክፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት8 |
10,000 ብር
|
9 |
የቆዳ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት9 |
50,000 ብር
|
10 |
የኮንስትራክሽን ት/ከፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት10 |
20,000 ብር
|
11 |
የማኑፋክቸሪንግ ት/ከፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት11
|
20,000 ብር
|
12 |
የጋርመንት ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች
|
ሎት12
|
50,000 ብር
|
13 |
የአውቶሞቲቭ ት/ከፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት13
|
50,000 ብር
|
14 |
የከተማ ግብርና ት/ከፍል እላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት15
|
20,000 ብር
|
15 |
የሆቴል ምግብ ዝግጅት፣ፀጉር ስራ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት15
|
40,000 ብር
|
16 |
የአይሲቲ ት/ከፍል አላቂ እና የጥገናና የስልጠና እቃዎች
|
ሎት16
|
15,000 ብር
|
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ከላይ በተጠቀሱት የዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ሰርትፍኬት/ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. በአቅራቢዎች መመዝገቢያ ላይ ራሳቸውን የመዘገቡ፣
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ በሚወዳደሩበት ሎት የተጠየቀውን ሰነድ ዋናውን ይዘው መም ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ሲፒኦ (CPO) ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል::
5. ተጫራች የሚያቀርቡት ዋጋ በእያንዳንዱ ላይ ቫትን ያጠቃለለ መሆን አለበት፡፡ ዋጋው ቫትን ያላጠቃለለ ከሆነ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ ፍሉድ የተጠቀመ ከሆነ እና በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች ተወዳድረው የሚያስገቡት ዕቃ ደረጃውን የጠበቀ መሆን አንዳለበትና በተወዳደረባቸው ሎቶች በሙሉ ከጨረታው ቀደም ብሎ የዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያልቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
8. ተጫራቾች የወሰዱትን የገዙትን/ የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ ካልተመለሰ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች የመደበኛ ጨረታ ሰነዱን ቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፐ/ፕስታ/ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፈውን ጠቅላላ ዕቃዎች በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ሊንዱስትረያል ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች በጨረታ ሲያሸንፍ 10(%) ፐርስንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
12. የጨረታው ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ጨኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ መ/ግ/ቡድን ይከፈታል።
13. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበዓላት ቀን እሁድና ቅዳሜ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
14. ኮሌጁ 20% ያሸነፉበትን እቃ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውነ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን ስ.ቁጥር 011 273 9712
ልዩ ስሙ፡ – ከመሳሰለሚያ ሠፈረ ሠላም ወደ መድሃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው አስፋልት ያኔት ኮሌጅ ከፍ ብሎ
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ