Your cart is currently empty!
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ መድኃኒቶች እና የላብራቶሪ እቃዎች፣ ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት-3 የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ልዩልዩ መሣሪያዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የህትመት ውጤቶችን ሎት 6 የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 7 ለሕንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና ሎት 8 ለሚኒስትሪሚንግ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም ኩኪስ፣ ቆሎ፣ ውሃ፣ ለስላሳ መጠጦች እና የተለያዩ ግብአቶችን ጨምሮ ሎት 9 የላዳ እና የፒክ አፕ የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 10-ለፕላንት፣ ማሽነሪ እና ለመሣሪያ እድሳት እና ጥገና ሎት 11-የሠራተኞች ክበብ /ካፍቴሪያ/ ጨረታ ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. በየዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TinNo) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ ለሎት1- 70,000/ ሰባ ሺ ብር ብቻ/ ለሎት 2- 9,968 /ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ስምንት ብር ብቻ/ ለሎት 3- 9,000 / ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ /ለሎት 4- 9,000/ ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ / ሎት 5 -5000 /አምስት ሺ ብር ብቻ / ለሎት 6 – 45,360/አርባ አምስት ሺ ሶስት መቶ ስልሳ ብር ብቻ/ ሎት 7- 15,800/አስራ አምስት ሺ ስምንት መቶ ብር ብቻ ሎት 8- 1,500 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ሎት 9- 1150 /አንድ ሺ አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ ሎት 10 – 3800 /ሶስት ሺ ስምንት መቶ ብር ብቻ/ ለሎት11- 13,200 /አስራ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል:: ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡
5. ጥቃቅን እና አነስተኛን በተመለከተ በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ከወረዳው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት እንደሚኖረው፣ ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት የተቋቋሙበትን ህጋዊ ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነዉ እሴትን ለሚጨመሩ /አምራች ለሆኑ/ ሥራ ዘርፎች ብቻ መሆኑንን እናሳውቃለን፡፡ ይሄንን ማስረጃ ካደራጀው አካል በደብዳቤ ተጽፎ ለማያቀርብ ተጫራች የጨረታ ሰነድ በነፃ እንደማይሰጠው እናሳውቃለን፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል፡፡
7. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ መሙላት አለበት፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለበት ፣የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት፣ ይህንን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተጫራቾች ከውድድሩ ወጪ ይሆናሉ፡፡
9. ይህ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን 10፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋውም በ10ኛው ቀን 11፡30 ይሆናል፡፡ ጨረታው በግልጽ የሚከፈተው በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
10. የጥገና ሥራዎችን በተመለከተ ማለትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ባለሙያዋች የወጣው እስፔስፍኬሽን የጥገና ሥራዎች በተመለከተ የሚወዳደሩት በጠቅላላ ድምር በአነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡ ሌሎች የጥገና ሥራዎች ወይም እስፔስፍኬሽን በአማርኛ የወጡ ሥራዎች ለየብቻ የሚወዳደሩ መሆኑንን እናሳውቃለን፡፡
11. የሠራተኞች ክበብ በተመለከተ የቤት ኪራይ ዋጋ 6000/ስድስት ሺ ብር ብቻ/ ሲሆን መሥሪያ ቤቱ ለመወዳደሪያ ያቀረባቸውን የምግብ፣ የሻይ ቡና እና የለስላሳ መጠጥ ዝርዝር ሁሉንም ዋጋ መሙላት ግዴታ ሲሆን ተጫራቾች የሚወዳደሩት አጠቃላይ ዋጋ ተደምሮ አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡ ዋጋ ዝርዝር አለመሙላት ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡ የሠራተኛ ክበብ በተመለከተ ዝርዝር መረጃው ከዋጋ መሙያው ሰነድ ጋር የተያያዘ መሆኑንን እናሳውቃለን፡፡
12.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ናሙናውን በመሥሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ ቢሮ 407 ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ /ተጫራች/ ከውድድሩ ወጪ ይሆናል፡፡ቋሚ እቃዎችን በተመለከተ ለማቅረብ ቀላል የሆኑትን በማቅረብ ወይም ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. መ/ቤቱ ጨረታውን ከውል በፊት 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 547 348 / 0115 460 29 / 0111 268 048 / 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ::
አድራሻ ፡– ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ሕንጻ ፊት ለፊት
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ