የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውል ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት የፋይናንስ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር 2018 . በጀት አመት ቁጥር 001/2018 አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተቁ

የእቃው አይነት

 

ሎት

 

የሚያሲዘው የብር መጠን እና ፐርሰንት

1

የደንብ ልብስ

 

1

5000.00 1 ፐርሰንት

 

2

የደንብ ልብስ ስፌት

 

2

3000.00 0.8 ፐርሰንት

 

3

አላቂ የጽዳት እቃዎች

 

3

5000.00 1 ፐርሰንት

 

4

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

 

4

5000.00 1 ፐርሰንት

 

5

አላቂ የቢሮ እቃዎች

 

5

4000.00 0.9 ፐርሰንት

 

6

የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች

 

6

3000.00 0.8 ፐርሰንት

 

7

የግንበኛ እቃዎች

 

7

3000.00 0.8 ፐርሰንት

 

8

የጥገና ስራዎች

 

8

4000.00 0.9 ፐርሰንት

 

9

ካፍቴርያ አገልግሎት

 

9

5000.00 1. ፐርሰንት

 

10

ቋሚ እቃ

 

10

6000.00 2. ፐርሰንት

 

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡

1. የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፣ 100,000 /ከአንድ መቶ ብር በላይ የሆነ ግዢና አገልግሎት ቫት ተመዝገቢ መሆን አለበት ተጨማሪ እሴት ታክስ( ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ተጫራቾች በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ የስራ ፍቃድ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው በዌብሳይት የተመዘገበ ለካፌ ተጫራች እና ለጥገና በአቅራቢነት ያልተመዘገቡ ቢሆኑም መወዳደር ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ስለሆነ ሰነድ በነጻ የሚሰጣቸው የተፈቀደላቸውን ዘርፍ ፍቃድ ኮፒ ማምጣት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

2. ተጫራች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነ መጓጓዣው በሚያቀርበው የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውሰጥ አካቶ ማቅረብ አለበት ነጠላ ዋጋውን ከነቫቱ ማስቀመጥ የሚቻለው የጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ቦታ ብቻ ሲሆን ከአንድ በላይ ዋጋ የሚያቀርቡበት ካለ ግን ኮፒ በማድረግ ሁለተኛ ገጽ ላይ ጽፈው አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ዋጋ ከነቫቱ እስቀምጡ ተብሎ በተጻፈው መሰረት የተቀመጠውን ዋጋ ከነቫቱ እንደሆነ ነው የምንወስደው፡፡ ምክንያቱም የአንዱ ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ ስለተጠየቀ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳነዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይንም የተወዳደሩበትን የጠቅላላ ዋጋ 0.5-2 ፐርሰንት ድረስ ከላይ በየሎቱ በተቀመጥው የብርና የፐርሰንት መጠን በኣዲስ ከተማ መሰናዶ / ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ካደራጃቸው ተቋም የጨረታ ማስከበሪያ ወይንም ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ ህጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. እንዲሁም ተጫራቾች ጨረታውን እነዳሸነፉ ከተገለጸላቸው በኋላ በሚጠቀሰው የገንዘብ መጠን ልክ አጠቃላይ የዋጋውን 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማምጣትና መዋዋል ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም አሸናፊዎች ከተገለጸላቸው በኋላ እቃው ጠፍቷል እቃው መግባት አይችልም ወይንም ገና ሊመረት ነው ወይንም ዋጋ ስለጨመረ እና እንዲሁም ተመሳሳይ ያልሆነ እቃ ለማስገባት መሞከር ተጠያቂነትን ያስከትላል

5. በተጨማሪም አነስተኛና ጥቃቅን ተጫራች ከሆኑ ላደራጃቸው ወይንም ዋስትና በአድራሻችን ጽፎ ደብዳቤ ለላከው ተቋም አስፈላጊውን የተጠያቂነት ፎርም ሞልተን እንደምናሳውቀው እና ለሚመለከተው አካል የምናስተላልፍ መሆኑን አውቀው ሁሉም ተጫራቾች ከወዲሁ የጨረታውን ጥራት ጠብቀው መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ፡፡

6. የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በመቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይኖርባቸዋል ፡፡

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድመው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ሳምፕል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ አውቆ ከመከፈቱ 3ቀን በፊት ማስገባት እንዳለበት እያሳወቅን ሳምፕል ለማይቀርብባቸው እቃዎች /ቤቱ ድረስ በመምጣት ሳምፕሉን በማየት የጥገና ስራዎችን እና በስፔስፊኬሽኑ መሰረት የተጠየቁ እቃችዎን ማቅረብ ይቻላል ሌላው በመዝጊያና በመከፈቻ ቀን የሚመጡ ሳምፕሎችን የማንቀበል መሆኑን በድጋሚ አስረግጠን እናሳውቃለን ፡፡

በተጨማሪ ደግሞ ናሙና ማቅረብ አስቸጋሪ ለሆኑ ወይንም ክብደት ላላቸው እቃዎች የሚወዳደሩበትን እቃ ስፔስፊኬሽን ወይንም ፎቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በተጨማሪ የንግድ ቦታ ድረስ በመሄድ የሚታይ ይሆናል፡፡

8. ለውድድር ያስገቡትን ናሙና ጨረታው እደተጠናቀቀ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሳይወስዱ ግን እስከ 6 ወር ድረስ ከቆዩ ላስገቡት ናሙና እና ማንኛውንም ነገር የማንጠየቅ እና ሃላፊነት መውሰድ የማንችል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምከንያቱም የአገልግሎት ቀኑ ሊያልፍና ሊበላሽ ሊቀደድ ስለሚችል፡፡

9. ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን፣ የምዝገባ ፍቃድ፣ ቫት፣ቲን፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ንግድ ፍቃድ ያደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰነድ ሙሉ የዋጋ ዝርዝራቸውን ጭምር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የሁሉንም ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱን በያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይመለሳል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ ከተፈቀደው ዋናና ኮፒ ሰነዶች ቀንሶ ማስገባት አይፈቀድም፡፡ እንዲሁም ዋና ላይ የሚገቡ ሰነዶች ኮፒ ላይ በስህተት ቢገባም ከኮፒ ውስጥ ሰነድ ወጥቶ እንደ ኦርጅናል ተከፍቶ ሊታይለት አይችልም፣ ሊወዳደርበትም የማይችል መሆኑን እንገልጻለን ፡፡ በሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ወይም ስርዝ ድልዝ መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡

10. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 330 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታ ላይ መገኘት ካልቻሉ ህጋዊ ወኪሎቻቸውን መላክ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስፈርቱን ካሟሉ ባይገኙም ያልተገኙትም ተጫራቾች ፖስታ ጭምር ይከፈታል፡፡ የጨረታ አከፋፈት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዝግ የሆኑ ቀናቶች ከገጠመ በሚቀጥለው ክፍት የስራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ይከፈታል ፡፡ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ወዲያውኑ በመቅረብ እቃውን ከማስገባቱ በፊት የአጠቃላይ ያሸነፈባቸውን እቃ ዋጋ አስር ፐርሰንት ብር (CPO)ከላይ በተጠቀሰው ስም ከባንክ በማሰራት ውል በመዋዋል ያሸነፉባቻውን እቃዎች ግዢ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች እንዳሸነፉ ከተገለጸላቸው በኋላ በትእዛዝ ከሚሰሩ እቃዎች ውጪ እቃ እጄ ላይ የለም ቀጠሮ ይሰጠን በሚል የተለያዩ ምክንያቶችን ማቅረብ አይፈቀድም ምክንያቱም እጅ ላይ ባለ እቃ ነው መወዳደር የሚችሉት ይህ ሳይሆን ቢቀርና ማሸነፋችሁ ከተገለጸ በኋላ እቃ ጠፍቷል ጊዜ ስጡኝ የሚል ጥያቄ አናስተናግድም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እንጠይቃለን ፡፡ሌላው ደግሞ ማንኛውንም እቃ 9፡00 ሰዓት በኋላ ጭነው ቢመጡ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምክንያቱም ጥራት ኮሚቴ አይቶ ፈትሾ ስለሚያስገባ ሰአት ስለሚያጥር ነው፡፡

11. /ምርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ወይንም 20 ፐርሰንት በላይ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

አድራሻ አዲስ ከተማ የክፍለ ሃገር አውቶብስ ተራ አጠገብ የሚገኘው አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011 276 3811/15/17

በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት /ቤት አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት

አጠቃላይ ማሳሰቢያ የካፌ የዴክስ፤ የመስኮትና፤ የቆርቆሮ፤ የላሜራ በሮች፤ የቧንቧ ስራዎች፤ አሸንዳና ጎራንዳዮ የመሳሰሉት በአንድ ጎራ ላይ የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ በአጠቃላይ ድምር ውጤት ነው አሸናፊው የሚገለጸው፡፡

እንዲሁም ለካፌ ተወዳዳሪዎች የቤት ኪራይ ብር 7000.00 (ሰባት ሺህ ብር) እና የዴስቲቪ ከፍያ በተጫራቹ የሚከፈል ነው፡፡

የካፌው አሸናፊ የሚለየው በጨረታ ሰነድ ላይ በቀረቡት ዝርዝር የአገልግሎት አቅርቦት ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ድምር ነው

የካፌ ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ካሸነፉ በኋላ ውሉ የሚያገለግለው ለአንድ አመት ነው፡፡

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት