የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኮንስትራክሽን ማቴሪያል (ስሚንቶ፣ ቆርቆሮ፣ ሚስማር ወዘተ)፣ የማዕድን ውጤት/ግባዓት (ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ጠጠር)፣ የደን ውጤት(ባህር ዛፍ እንጨት)፣ ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር ወዘተ)፣ ጽ/መሳሪያ (ኮፒ፣ ወረቀት፣ እስክርቢቶ ወዘተ)፣ የመኪና ጎማ፣ ሞተር ሳይክል እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የመኪና ሠርቪስ እና ፈርኒቸር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

 Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 01/2018

በደቡብ ኢ/ክ መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጨረታውን የሚያቀርበው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጠበላ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች

  • ኮንስትራክሽን ማቴሪያል (ስሚንቶ ቆርቆሮ፡ ሚስማር ወዘተ)
  • የማዕድን ውጤት/ግባዓት (ድንጋይ፡ አሸዋ ጠጠር)
  • የደን ውጤት(ባህር ዛፍ እንጨት)
  • ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር ወዘተ) 
  • ጽ/መሳሪያ (ኮፒ ወረቀት እስክርቢቶ ወዘተ)
  • የመኪና ጎማ ፡ሞተር ሳይክል እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ የመኪና ሠርቪስ እና
  • ፈርኒቸር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና በሚመለከተው አካል ድርጅታቸው የተመዘገበ ሆኖ የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈሉና ሌሎች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቦ መቅረብ አለባቸው።

  1. አቅራቢነት/ በኦንላይን e-GP በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ።
  2. ተጫራቾች መጫረቻቸውን /መወዳደሪያ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 ሶስት መቶ ብቻ ጠበላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ የከፈሉትን ደረሰኝ ኦሪጅናል ይዘው ከግዥ ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ CPO/ካሽ/ 20,000 ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ማቅረቢያ ሠነድ ሲዘጋጅ በቀረበው ዕቃዎች ዝርዝር መሰረት ሠነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ኦርጅናሉን ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦርጅናሉን በተለያየ ሦስት ፖስታ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎኘ ውስጥ ሆኖ CPOን ጨምሮ ሦስቱንበአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ በጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ ህንፃ 3 ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ (ከወጣበት ከ15 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ የጨረታ ሳጥን ክፍት ቆይቶ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላትና የመ/ቤቱ ተወካዮች በተገኙበት ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ግለሰብ/ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከመ/ቤት ጋር የውል ስምምነት ይፈጽማል።
  8. ዕቃ ንብረት ማራገፊያ ቦታ በጠበላ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
  9. ሁሉቱም ወገኖች ውሉን ተግባራዊ ለማድረግ የማይቀርቡበት ሁኔታ ቢከሰት የኢት/ያ / ፍትሀብሔር ሕግ በሚያዘው መሠረት የሚፈፀም ሲሆን ሌሎች በውሉ አፈፃፀም መሠረት አስፈላጊ መብትና ግዴታዎችን የሚያካትት ይሆናል።
  10. ኛውም ግዥ የሚፈፀመው በነጠላ ዋጋ ይሆናል።
  11. በጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ አቅርበው ያሸነፉ አሸናፊ ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ በሁለተኛ ደረጃ ያሸነፈው በመጀመሪያው ዝቅተኛ ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ ከሆነ ማቅረብ ይችላል፤፤
  12. የከተማው ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት – የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0972612664 /0940318347 / 0910796224

በደቡብ ኢ/ክ መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ

አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት