ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ህትመት ስራዎች፣ የቤት ጥገና፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ፣ የጉልበት አገልግሎት ግዢ እና የህንጻ መሳሪያዎች ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ o6 ጤና ጣቢያ ለእያንዳንዱ ሎት መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ብር

  • 1-የጽህፈት መሳሪያ (21000.00) ብር
  • 2- የደንብ ልብስ (22500.00)ብር
  • 3-የጽዳት እቃዎች (25000.00) ብር
  • 4-ቋሚ እቃዎች (27500.00) ብር
  • 5-ህትመት ስራዎች (18000.00) ብር
  • 6-የቤት ጥገና (10000.00) ብር
  • 7-የኤሌክትሮኒክስ ጥገና (5000.00) ብር
  • 8- የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ (6000.00) ብር
  • 9-የጉልበት አገልግሎት ግዢ 6000.00) ብር
  • 10 የህንጻ መሳሪያዎች ግዢ (10000.00) ብር

በኮ////የወ/6//ጣቢያ በጨረታ ቁጥር 001/2018 .

  • የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች የደንብ ልብሶች የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎችን፤ የህትመት ስራዎችን ልዩ ልዩ የአገልግሎት ግዢዎችን ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

 ስለሆነም።

1. በመንግስት እቃ አቅራቢነት ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው።

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ግብር ከፋይ ቲን የምዝገባ ወረቀት ያላቸው ሆነው በዋጋ ዝርዝር ላይ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው።

4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየሎቱ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 47 መግዛት ይችላሉ።

5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ለማቅረብ የማይመቹ እቃዎችን በፎቶ እና በካታሎግ ማቅረብ ወይም መስሪያቤቱ ድርጅቱ ድረስ ለሚልካቸው ኮሚቴዎች ተፈላጊ እቃዎችን ማሳየት ይኖርባችኋል።

6ኛ. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መሙላት አይቻልም።

7ኛ. ገዢው የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ድረስ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እና ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ 4 ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9ኛ. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሳል።

10ኛ. አሸናፊዎች በሰነዱ ውስጥ በተገለጸው ጊዜ ገደብ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ያሸነፉበትን 10% ሲፒኦ በማሰራት ውል መዋዋል አለባቸው።

11ኛ. ጨረታው የሚከፈተው 11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 430 ላይ በተቋሙ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።

12.ተጫራቾች የሚያቀርቡአቸው እቃዎች የአገልግሎት ጊዜአቸው የሚያበቃበት ቀን ቢያንስ ከአንድ አመት በላይ መሆን ይኖርበታል።

13. የእያንዳንዱ ሎት ኦርጂናል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ መታሸግ ይኖርበታል

14. መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. እስቶር እስከ ማስገባት ድረስ ያለውን የማጓጓዣና የጉልበት ወጪ ተጫራቹ ይሸፍናል።

16ኛ. የጨረታ ማስከበሪያው በትክክል የተቋማችንን አድራሻ መግለጽ ይኖርበታል።

17ኛ. ከአነስተኛ እና ጥቃቅን /ቤት የሚጻፉ ደብዳቤዎች በትክክል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል። እንዲሁም ደብዳቤዎቹ በጽ/ቤቱ ሃላፊ ፊርማ እና ቲተር መውጣት ይኖርበታል።

18ኛ. በሚጫረቱበት እቃ ላይ እሴት ለሚጨምሩ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ልዩ ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።

19ኛ. የጨረታው የስራ ቋንቋ የፌደራሉ የስራ ቋንቋ(አማርኛ) መሆን አለበት።

20. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፣ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ

ብሎ ክፍለከተማው አጠገብ ወይም ፖስታ ቤት ፊትለፊት።

ለበለጠ መረጃ ስስከ ቁጥር፡– 011 833 6993

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06  ጤና ጣቢያ