በሁርሶ የሚገኘው የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 05, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሜ የወጣ የመኪና ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

በሁርሶ የሚገኘው የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የምታሟሉ በሙሉ ሰነዱን በመግዛት (አንድትጫረቱ) ማሰልጠኖችን ይጋብዛል፡

  • የመኪና አከራይ ፍቃድ ያላቸው።
  • ለሁሉም ተወዳደሪ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቫት እና ቲን ነምበር ያላቸው ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የታደሰ 3 ወገን ኢንሹራንስ በወንበር ቁጥር ልክ ያለው፡፡
  • የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የምችሉ እና ሌሎች ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው
  • ሰነዱን ድሬዳዋ ነምፔር ዋን አከባቢ በሚገኘው መኮንኖች ክበብ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
  • በጥቅል 30,000 C.P.O በማሰልጠኛው ስም SHORT COURSE OFFICER CADET TRAINING SCHOOL ብለው ማሰራት ይቻላል። በተናጠል ደግሞ በሠንጠረዥ ውስጥ ባለው ይሆናል።

መለያ

የአገልግሎት ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

ሎት 01

የተለያዩ የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖች

10,000 ብር በአንድ መኪና

  • ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰው የተለያዩ የስርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የመኪና ኪራይ ለማቅረብ መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚታሟሉ በሙሉ ሰነዱን በመግዛት እንዲትጫረቱ ማሰልጠኛችን በደስታ ይጋብዛል፡፡
  • በኢፌዴሪ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገፅ ተመዝጋቢ የሆኑ
  • አነስተኛና ጥቃቅን ካደራጃቸው ማህበር ደብዳቤ እና /ቁጥር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እና
  • በማጭበርበር ወንጀል ያልተከሰሱ እና በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ፍርማና ማህተም የተደረገበት 1 ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾችፋይናንሻል ከመከፈቱ በፊት በዕለቱ ከረፋዱ 400 ላይ የምወዳደሩበትን መኪና በማቅረብ የቴክኒክ ፍተሻ እንዲደረግ ማድረግ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው ጳጉሜ 03/2107 / እስከ መስከረም 13/01/2018 / ማክሰኞ ዕለት ከሰዓት 800 ሰዓት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በዚያኑ ድሬዳዋ ነምፔር ዋን አከባቢ በሚገኘው መኮንኖች ክበብ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 13/01/2018 . ማክሰኞ ዕለት 830 ይከፈታል፡፡
  • ሰነዱን ድሬዳዋ ነምፔር ዋን አከባቢ በሚገኘው መኮንኖች ክበብ በስራ ሰዓት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት CPO ማስያዝ አለበት፡፡
  • የጨረታ ማስከበርያው ከአሽናፊ ድርጅት ጋር ውል ስናስር ለተሸናፊ ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር: 09 75 29 99 04 / 09 11 04 40 21 በቀጥታ መስመራችን በቢሮ ስልክ 025 447 0157 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ /ቤት

ሁርሶ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *