በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሕትመት አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ቋሚ እቃ፣ የድንኳን ኪራይና የሞንታርቦ ኪራይ እንዲሁም የዲኮር ሥራዎች በመንግሥት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 08 ፋይናንስ /ቤት 2018 በጀት ዓመት አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሕትመት አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ቋሚ እቃ፣ የድንኳን ኪራይና የሞንታርቦ ኪራይ እንዲሁም የዲኮር ሥራዎች በመንግሥት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ሕጋዊ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ፖስታ በወረዳው ፋይናንስ ግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 230 – 830 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ማለትም በየሎቱ፡

  • ሎት 1. 29,060.00 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ስልሳ ብር ብቻ)
  • ሎት 2. 7,316.00 (ሰባት ሺህ ሶስት መቶ አስራ ስድስት ብር ብቻ)
  • ሎት 3. 17,700.00 (አስራ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ብር ብቻ)
  • ሎት 4. 4,110.00 (አራት ሺህ አንድ መቶ አስር ብር ብቻ)
  • ሎት 5. 12,565.00 (አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አምስት ብር ብቻ) በጣም
  • ሎት 6. 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 7. 6,300 (ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የእያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና ዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው::

6. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በየሎቱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል በወረዳ 08 በፋይናንስ /ቤት ቢሮ ቁጥር 24 መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው 11ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ /ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ርክክብ የሚፈጸሙበት በራሳቸው ትራንስፖርት ሆኖ በወረዳው /ቤት ንብረት ፍል ነው፡፡

10. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ መሞከር በሕግ ያስጠይቃል፡፡

11. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

12. /ቤቱ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ተጫራቾች ከአንድ በላይ ሎቶች መወዳደር ከፈለጉ የየሎቱን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 08 የፋይናንስ /ቤት በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 666 1614 ደውለው ያነጋግሩን፡፡

አድራሻ፡ፊጋ ሰፈር ከበሻሌ ንግድ ባንክ ወደ ሰሚት በሚወስደው አስፓልት መንገድ ሳፋሪ /ቤት ከመድረሶዎት በፊት መሲ ሕንጻ ወረድ ብሎ፡፡

በለሚ ኩራ /ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ /ቤት