Your cart is currently empty!
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ አልባሳትን፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የህትመት የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣የደንብ አልባሳትን ቋሚ ዕቃዎች እና የህትመት የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከሎት 1-5 ለተጠቀሱት ዕቃዎችና የአገልግሎት ግዥ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን ነጥቦችበሚገባ ተረድተው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በሎት በእያንዳንዱ ሎት በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።
ተ.ቁ |
ሎት |
የግዥው ዓይነት |
የሲፒአ መጠን በብር |
የመዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
ሎት 1 |
የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ |
20,000.00 |
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.ሰዓት 4፡30
|
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.ሰዓት 5፡00
|
2 |
ሎት2 |
የጽዳት ዕቃዎች ግዥ |
35,000.00 |
||
3 |
ሎት3 |
የደንብ ልብስ አልባሳት ግዥ |
20,000.00 |
||
4 |
ሎት4 |
የቋሚ ዕቃዎች ግዥ |
10,000.00 |
||
5 |
ሎት5 |
የህትመት አገልግሎት ግዥ |
5,000.00 |
1. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት
- በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የግብር ከፋይ መለያ TIN N.O./ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
3. ከአነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት በአምራችነት ተደራጅታችሁ መወዳደር የምትፈልጉ ካላችሁ ካደራጃችሁ አካል በጽ/ቤት ኃላፊ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ማምጣት አለባችሁ፡፡ የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት ዕቃ የጨረታ ሰነድ መግዣና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት የአንዱን መለኪያ ዋጋ 15% የተ.እ.ታ. ጨምሮ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን የተለያዩ ኤንቨሎፖች ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶች ለያይተው በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።በተጨሪም አንድ ኮፒ በማሸግ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ነው።
8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣበት ማስታወቂያ መሰረት ከላይ በሰንጠረዥ በተገልጸው ቀን እና ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከመገናኛ ጎሮ አደባባይ ፍሊት ስቶን ከጎሮ ሳይት ሳይደርሱ ከድልድዩ በስተቀኝ ያገኙታል።
ስልክ ቁጥር 011-8-664855
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት