በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን ግዥ አገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 07, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 01/2018

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ 2018. በጀት ዓመት መግዛት የሚፈልጋቸውን

  • ሎት 1የተለያዩ የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  •  ሎት 2የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  • ሎት 3የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  • ሎት 4የህትመት ጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  • ሎት 5ጥገና የሚደረግላቸው ኮንፒውተር፣ ፕሪንተር፣ የፎቶኮፒ ማሽኖችና ሌሎች የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  • ሎት 6ቋሚ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
  • ሎት 7ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
  • ሎት 8የተሽከርካሪ የኪራይ አገልግሎትና የመኪና እና የጄኔሬተር እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
  • ሎት 9የመድሀኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
  •  ሎት 10 የተለያዩ ቋሚ አላቂ የካፌ እቃዎች (የሻይ ብርጭቆ፣ የቡና ስኒ፣ ረከቦት፣ ትሪ እና የተለያዩ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
  • ሎት 11 የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
  • ሎት 12የሙሉ ህንጻ የውጭ ግድግዳ የቀለም ቅብና የተለያዩ እድሳቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 ብቃት ያላቸው በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ አገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፣

1.     1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግን አስ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 (ፋይናንስ) ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 430 ሰዓት በወ/ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል፤ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዐል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጪና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

7. የዘገየ ጨረታና በመክፈቻው ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

8. ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናቶች የተወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማስገባት አለባቸው ናሙና ያልቀረበበት ጨረታ ዋጋ አይኖረውም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ የመ/ቤቱ ስልክ 011-8-54-9237

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ