በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ፅህፈት መሳሪያ፣ ህንፃ መሳሪያ፣ የግንባታ ድንጋይ አሸዋ፣ የግንባታ እንጨት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተር ሳይክል፣ የባህል አልባሳት፣ ህትመት፣ የግንባታ ብሎኬት፣ የእንስሳት መድኃኒት፣ የወለል ምንጣፍ እና ቴራዞ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2018 ዓ.ም

  1. ሎት 1 ፅህፈት መሳሪያ
  2. ሎት 2 ህንፃ መሳሪያ
  3. ሎት3 የግንባታ ድንጋይ አሸዋ
  4. ሎት4 የግንባታ እንጨት
  5. ሎት5 ኤሌክትሮኒክስ
  6. ሎት6 ሞተር ሳይክል
  7. ሎት7 የባህል አልባሳት
  8. ሎት 8 ህትመት
  9. ሎት 9 የግንባታ ብሎኬት
  10. የእንስሳት መድኃኒት
  11. ወለል ምንጣፍ
  12. ቴራዞ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ማቴሪያሎችን በመደበኛና በተራዶ ፣በማዘጋጃ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን ነበር ያላቸው )
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በተመሰከረለት ባንክ CPO ወይም ህጋዊ የባንክ ማረጋገጫ ያለው ለእያንዳዱ ሰነድ ማስያዣ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ ብር ለእያንዳዱ የሰነድ አይነት በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመክፈል ከግዥ/ን/ አስ/ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  7. ማንኛውም ተጫራች በማረቆ ልዩ ወረዳ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ባለው ግዥ/ን/አስ/ ስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  8. ጨረታው ከወጣበት ተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 5 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥ/ን/አ/ ቢሮ ቁጥር 5 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ድረስ የሚያቀርቡ መሆኑን እንገልፃለን።
  9. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  10. ለበለጠ መረጃ፡- መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 0464650046 መረዳት ይቻላል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት