Your cart is currently empty!
በምስራቅ ወለጋ ዞን የዋማ ሀገሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ግልፅ ጨረታን አውጥቶ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ወለጋ ዞን የዋማ ሀገሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ግልፅ ጨረታን አውጥቶ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ አይነቶች፡_
- የፅሕፈት መሣሪያ፣ የፅዳት መሣሪያ፤
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ለቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ዕቃዎች የሚውል፤
- የቋሚ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮች ዕቃዎች በግልፅ
- የግንባታ ዕቃዎች፣ መኪና መለወዋጫ እና የሞተር መለወዋጫ እቃዎች
- ለድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ዩኒፎርም እና ሞተር ግዥ ባለ 125 እስከ 175 ሲሲ
በዚህም መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የ2017/8 ዓ.ም ግብር ስለመከፈሉ ከጉሙሩክና ገቢዎች ባለሥልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በንግድ ሥራ ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የVAT ተመዝጋቢ የሆነና TIN No. ያለው
- የሚያስፈልግ ሰነድ/specification/ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በዋማ ሀገሎ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ከወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር በአካል ቀርቦ መውሰድ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአንድ ሰነድ በጥሬ ገንዘብ ብር 5000 (አምስት ሺህ) በ64 ሞዴል ማስያዝ የሚችልና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው በውል ከታወቀ ከ5 ቀን በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
- ለውል ስምምነት ማስከበሪያ የሚውል ከጠቅላላው ግዥ ገንዘብ ውስጥ 10% ማስያዝ የሚችልና የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አሸናፊው በውል ከታወቀ ከ10 ቀን በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አሸናፊው በጊዜና በጥራት ካላቀረበ የውል ማስከበሪያ ገንዘብና የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ የሚወረስ ይሆናል።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፤ እንዲሁም በአካል ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ እስከ ዋማ ሀጋሎ ወረዳ ገ ጽ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች ማንኛውም ሰነድ ኦርጂናልና ኮፒውን፤ የቴክኒክ ዋናና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንስ ፖስታ ዋናና ኮፒውን ማስረጃ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁሉንም በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆ ሲሆን በ12/01/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ይዘጋል።
- ጨረታው ለ15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ12/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ተወዳዳሪው ወይም ሕጋዊ ተወካይ በተገኙበት በዋማ ሀጋሎ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት)ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪው ተወካዩ ሰነድ አስገብቶ በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኝም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
- ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-57 447 0196 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
በምስራቅ ወለጋ ዞን የዋማ ሀገሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Materials cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Furniture cttx, Electromechanical and Electronics cttx