Your cart is currently empty!
በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01
በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከመደበኛ በጀት
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ በሲፍትኔት ካፒታል በጀት
- ሎት 2 የግንባታ እቃዎች፣
- ሎት 3 ሲሚንቶ፣
- ሎት 4 እንጨት፣
- ሎት 5 ድንጋይ አሸዋና ጠጠር፣
- ሎት 6 በወልዲያ ከተማ አስተዳደር 07 ቀበሌ አደንጉር ገብርኤል ልዩ ቦታው መንደቅ ከመሬት በታች የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ግንባታ የእጅ ዋጋ፣
- ሎት 7 በጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር 05 ቀበሌ ልዩ ስሙ አምባላጫ የመስኖ ካናል ማራዘም ግንባታ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ስመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሎት በተሰጠው እስፔሲፊኬሽን መሰረት በማቅረብና ማጓጓዝ፤ የመጫኛና የማውረጃ ወጭዉን በራሳቸው በመሸፈን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎችን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ከሎት 2 (ሁለት) እስከ ሎት 5 (አምስት) ድረስ ያሉትን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የማስገቢያ ወይም የማራገፊያ ቦታዎች ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውል በመውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉበትን እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸው ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ከፒ ማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ስለሚያቀርቧቸው እቃዎች ትክክለኛነቱን እና በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት ስለመቅረቡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ ተረጋግጦ መስሪያ ቤቱ የሚረከብ ይሆናል።
8. የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ በድርጅትዎ ማህተም ተረጋግጦ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 1(አንድ) ለተከታታይ 15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16( በአስራ ስድስተኛው ) ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡00 በግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። ከሎት 2 (ሁለት) እስከ ሎት 7 (ሰባት) ያሉት ሎቶች ለተከታታይ 30 (ሰላሳ) ቀን አየር ላይ ውሎ በ31 (ሰላሳ አንድኛው) ቀን 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ሰዓት በግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። ነገር ግን የሁለቱም የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ ሁሉም ጨረታዎች ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ተሸጋግሮ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
10. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላችሁ ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ አለባችሁ።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት 30,000.00 ( ሰላሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ CPO ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
12. የጨረታ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊው ውል ከወሰደ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይለቀቃል ፣ አሸናፊዉ የውል ማስከበሪያ 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ CPO እና በሁኔታ ላይ ባለተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ኦርጅናልን በማስያዝ በጉ/ወ/ፍትህ/ጽ/ቤት በኩል ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ ወይም እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት መ/ቤቱ አያስተናግድም፤ ነገር ግን እቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፅማል።
14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 431 0736 ወይም 033 540 0721 ደውለው ወይም የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።
የጉባ ላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት