Your cart is currently empty!
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ለሚገኙ ሴከተሮች አላቂ የጽዳት፣ ኤሌክሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እና የደንብ ልብስ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 08, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ለሚገኙ ሴከተሮች አላቂ የጽዳት፣ ኤሌክሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እና የደንብ ልብስ
ደንብ መመሪያ Bidders instruction
ሀ. የተወዳዳሪዎች መመሪያ
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ
ሀ. የዘመኑን ግብር በመክፈል የ20107/18 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ
የገ/ኢ/ልማት ሚኒስቴር የዕቃ ዓቅራቢነት የምዝገባ ማስረጃ
ሐ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስናና የብክነት ድርጊቶች ነጻ የሆኑና ቤፌዴራልና በክልል የወጡትን የግዢ ደንቦች በማክበር ሰነዱ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነውበት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛም ተጫራች ጨረታውን በህገወጥ መንገድ ሊያራምድ የሞከረ ከጨረታው ወጪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ በሚካሄዱ ጨረታዎች ላይ እንዳይሳተፍ ተደርጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል ።
- ተጫራቾች ወደጨረታው ለመቅረብ ግዴታዎቻቸውን የተወጡና የተጠየቀውን ስፔስፊኬሽን በማሟላት የወትቱን ገበያ ያገናዘበ ዋጋ ያቀረቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ቤቱ ባቀረበው ዕቃ ዝርዝር በሙሉ ወይም በሚፈልገውም የዕቃ ዝርዝር ላይ መሠረት ይችላሉ እንጂ ተጫራቹ የተወሰነ ዕቃ ለይቶ ማቅረብ አይችልም።
- የተወዳዳሪዎች ሀሳብ ሰነድ ሲቀርብ የዕቃው ስፔስፊኬሽን፣ የዕቃው አይነት፣ የተመረተበት ሀገር ስም፣ የዕቃው መለያ ሞዴል ቁጥር፣ የተመረተበት ዓመተምህረት ስፔስፊኬሽን ላይ መግለፅ አለበት።
- አሸናፊ ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ከጨረታው ዕቃ 60% ገቢ ካደረጉ በኋላ ከጠቅላላው ዋጋ 30% ብቻ መጠየቅ ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ አይነት የነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የሚቀርበው ዋጋ የወቅቱን አካባቢ ገበያ ያገናዘበ መሆን ይገባዋል።
- የዕቃው ሞዴል ወይም ስዕል ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ይቀርባል።
- መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ጨረታ ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- አሸናፊ ተጫራች የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይወረሳል።
- የጨረታው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዞ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይቀርባል።
- የሚቀርበው ሰነድ ሙሉ አድራሻ የተጻፈበት ሆኖ በሚመለከተው ባለስልጣን የተፈረመበትእና በማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት።
- የጨረታውን ሰነድ ከውሰርቢ ወረዳ ገንዝብ አንድ /1/ ከጳጉሜ 03/2017 እስከ 19/01/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ ጨረታውን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።
- ሰነዱን ለመመርመርና ለመገምገም የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ መስሪያ ቤቱ ተጫራቾቹ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ላይ መግለጫ መጠየቅ ይችላል።
- ጨረታውን በመመርመር ሂደት ላይ የተገኘውን የሀሳብ ስህተት ማስተካከል ይቻላል። ድርጊቱ ወዲያው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ለቀረበ ክፍል ይገለጽለታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የውድድር ሀሳብ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጨረታ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ውስጥ ከግዥው ዋጋ ላይ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼከ ወይም /CPO/ በማቅረብ የግዢ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ማስከበሪያ አሸናፊው ከታወቀ ለተሸናፊዉ ይመለስለታል።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የውል ማስከበሪያውን ገቢ አድርገው ከጨረሱ በኋላ ይመለስላቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከፈጸሙ በኋላ በ1ዐ ቀን ውስጥ ዕቃውን አጠናቀው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ዋጋ የጨረታው ውጤት ከተነገረበት ቀን አንስቶ ዕቃውን ማስረከቢያ ቀን ድረስ ያለምንም ለውጥ መቆየት አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፉ ዕቃዎቹን በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ማውጫና ማውረጃ ችለው የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሚቀርቡት ዕቃዎች የተቀደዱ፣ የተሰበሩ፤ የተበላሹና ከአገልግሎት ውጪ ከሆኑ መስሪያ ቤቱ አይቀበላቸውም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ የሰነድ መሸጫ የማይመለስ 500 ብር ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 82 15 21 በዚህ ስልክ ቁጥር ደውለው የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx