Your cart is currently empty!
በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልከ ኖኖ ክ/ከተማ የቤሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶችና ለማዘጋጃ መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 04, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልከ ኖኖ ከ/ከተማ የቤሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሲከተር መ/ ቤቶችና ለማዘጋጃ መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ዝርዝር ሁኔታዎች
ይህ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት, የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ አንደኛ (1) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 ላይ በመክፈል በቤሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሁለተኛ(2) ፎቅ ቁጥር 10 ላይ በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የተጫራቾቾ ግዴታዎች
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) ባንክ ስለመኖሩ ከባንኩ የተጻፈለት ደብዳቤ ጋር መያያዝ CPO (ሲፒኦ)ን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና (10%)ማስያዝ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 29/12/2017 ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እስከ ከቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ብቻ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮችና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በቤሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት አስተባባሪ ቢሮ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 15 82 84 75/ 09 20 12 83 66
የቤሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት