በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አ አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 01, 2025)

 Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

 ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዢው መለያ ቁጥር ግልጽ ጨረታ 01/18

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አ አስተዳደር ጽ/ቤት ስር ላሉት ጽ/ቤቶች 01/18 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን

  • ሎት-1 የፅህፈት እቃዎች
  • ሎት-2 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት-3 ፈርኒቸር ጥገና
  • ሎት-4 ኤልክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት-5 ቋሚ እቃ ግዢ
  • ሎት-6 መስተንግዶ አገልግሎት ግዢ
  • ሎት-7 ደንብ ልብስ አገልግሎት
  • ሎት-8 ቋሚ አላቂ እቃዎች
  • ሎት-9 የህትመት አገልግሎት
  • ሎት-10 የጉልበት አገልግሎት
  • ሎት-11 የጭነት መኪና አገልግሎት
  • ሎት-12 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት-13 ምርጥ ዘር ግዢ

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር ለሎት 1 ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት3 ብር 9,000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 4 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 5 ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 6 ብር 9,000.00(ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 7 ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 8 ብር 8,000(ስምንት ሺህብር ብቻ) ለሎት 9 ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 10 ብር 5,000  (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 11 ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 12 ብር 8000(ስምንት ሺህ ) ብቻ ለሎት 13 ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብቻ) በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 13 ጀ/አ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወ/13/ጀ/ ፋይናንስ ጽ/ቤት ጀሞ አንደኛ በር በሚገኘው ሳባ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 ላይ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 601 በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 601 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፤ ሎት 2፤ ሎት 5፤ ሎት 6 እና ሎት 7 ሎት 8 ሎት 9 ሎት 13 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ ፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት በፊት እና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዢ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ

አድራሻ ጀሞ እንደኛ በርሳባ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አ አስተዳደር ጽ/ቤት