Your cart is currently empty!
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አባይ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አባይ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1 የደንብ ልበስ፣
- ሎት 2 ፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 3 ህትመት፣
- ሎት4 ህክምና እቃዎች፣
- ሎት 5 ትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣
- ሎት 6 ፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት 8 ለተለያዩ ጥገናዎች፣
- ሎት 9 ቋሚ ዕቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ አገልግሎት ብቃት ባላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል ፡፡
በዚህም መሰረት፡–
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎተ ያላቸው ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ቲን ያላቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለሎት 1 የደንብ ልብስ 30,000 ለፅህፈት መሳሪያ ብር 40,000፣ ለህክምና ዕቃዎች 1,000 ሎት 5 ትምህርት መርጃ መሳሪያዎች 18,000 ሎት 6 ለፅዳት እቃ 32,000፣ ሎት 7 ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 2,000 ሎት 8 ለተለያዩ ጥገናዎች 7,000 ለቋሚ እቃ ግዢ ብር 7,000 እና ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 7,000 ለፈርኒቸሮች 7,000 ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አባይ የመ/ደ/ት/ቤት ቢ.ቁ 13 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ተወዳዳሪዎች አላቂ ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ በሙሉ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለቋሚ ዕቃዎች ግን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንደንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ጀሞ ቁ የጋራ መኖሪያ ቤት አጠገብ ከኪሩ ባርና ሬስቶራንት ፊትለፊት የኮብል እስቶን መንገድ 300 ሜ ገባ ብሎ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011-835-3392/97
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አባይ የመ/ደ/ት/ቤት