Your cart is currently empty!
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ እቃዎች ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመት፣ መስተንግዶ፣ የቢሮ ማሽን ጥገና፣ የቢሮ እና የቢሮ እቃዎች ጥገና፣ የመኪና ኪራይ፣ የአትክልት ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት
- አላቂ የቢሮ እቃዎች ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- ህትመት፣
- መስተንግዶ፣
- የቢሮ ማሽን ጥገና፣
- የቢሮ እና የቢሮ እቃዎች ጥገና፣
- የመኪና ኪራይ፣
- የአትክልት ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
3. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የሚያሳይ የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት በየሎቱ አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም የተዘጋጀ CPO ከመወዳደርያ ሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
የሚያስይዙት የሲፒዮ መጠን |
|
1 |
ሎት1 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
10.000 |
|
2 |
ሎት2 |
ልዩ ልዩ መሣሪያዎች |
3.000 |
|
3 |
ሎት3 |
የፅዳት እቃዎች |
15.000 |
|
4 |
ሎት4 |
የደንብ ልብስ |
5.000 |
|
5 |
ሎት5 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
15.000 |
|
6 |
ሎት6 |
ህትመት |
2000 |
|
7 |
ሎት7 |
መስተንግዶ |
1.000 |
|
8 |
ሎት8 |
የቢሮ ማሽን ጥገና |
1.000 |
|
9 |
ሎት9 |
የቢሮ እና የቢሮ እቃዎች ጥገና |
1.000 |
|
10 |
ሎት10 |
የመኪና ኪራይ |
1.000 |
|
11 |
ሎት11 |
የአትክልት ዘር |
1.000 |
4. ጨረታው ጋዜጣው ላይ በወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት የተወከሉበትን የውል ማስረጃ እና መታወቂያ በመያዝ በአ/ክ/ከ/ወ/7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻው በታሽገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው ፡፡
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 122 2848 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡– አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ ሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ማሳሰቢያ፡–ሳምፕል የተጠየቀባቸው እቃዎች ጥራት የሚወሰነው በሳምፕሉ መሰረት ይሆናል።
ነገር ግን የቋሚ ዕቃዎች ጥራት የሚወሰነው በቀረበው ፎቶ እና እስፔስፊኬሽን መሰረት ይሆናል፡፡
ለጥገና፣ መስተንግዶ የመኪና ኪራይ የአትክልት ዘር ሳምፕል አይኖረውም፡፡
ተጫራቾች ለአንድ እቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት