Your cart is currently empty!
በአራዳ ክ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የሚያስፈልገውን ንብረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የሚያስፈልገውን:-
- ሎት -1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት -2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት -3 አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
- ሎት – 4 የተለያዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት – 5 የፕላንት ማሽነሪ እና መሣሪያ መግዣ፣
- ሎት -6 የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት -7 ቋሚና አላቂ ጽዳት እቃዎች፣
- ሎት -8 ህትመት፣
- ሎት -9 ለህንፃና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች መግዣ
- ሎት – 10 ፕላንት ማሽነሪ ጥገና፣
- ሎት – 11 የሚሸጥ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ቅድሚያ ሟማላት ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ያላቸው፤ TIN NO የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል በተጨማሪም በመንግስት ግዥ ያልታገዱ።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በፖስታ አሽገው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር) በሕጋዊነት ከተረጋገጠ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል ኦሪጅናል እና እንዲሁም የቴክኒካል የኦሪጅናል ኮፒ በመለየት ተሟልቶ በማሸግ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ አድራሻ በመፃፍ ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ት/ቤቱ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅፅ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል።
6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመከፈቻ እለቱ በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ናሙና ያልቀረበበት፣ የዘገየ፣ የጨረታ በመክፈቻ ሂደት ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ተሟልቶ ያልመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። በጨረታ ሰነድ ክፍል 4.6.9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልተው ያላቀረቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዣ እና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡበት እቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም።
10. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም። መስሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: አራት ኪሎ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎን ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ገባ ብሎ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011-232-866 ይደውሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት