Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የህብረት 1ኛ ደ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የጥበቃ ፅዳትና መምህራን ደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቆች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የትምህርት እቃዎች፣ የላብራቶሪ ኬሚካል ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፃህፍት፣ ቋሚ ዕቃዎች እንዲሁም የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና ፎቶኮፒ ማሽን ጥገና ስራዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018 በጀት ዓመት
በአዲስ አበባ አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የህብረት 1ኛ ደ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የጥበቃ ፅዳትና መምህራን ደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቆች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣የትምህርት እቃዎች፣የላብራቶሪ ኬሚካል ዕቃዎች፣ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፃህፍት፣ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። እንዲሁም የኮምፒውተር፣ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ ማሽን ጥገና ስራዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ መስፈርት ከዚህ በታች እንደሚመለከተው ይሆናል
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢትን ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑ የታደሰ ግብር ከፋይ መለያ ተመዝጋቢ የሆነ
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህብረት ችቦ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋ/ግ/ን/አስ/ቡድን/አስ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ በየሎት 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የገዙትን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው በመፃፍ ለየብቻ በማዘጋጀት ፊርማ ማህተም በማሳረፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10ኛ ቀን የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የህብረት ችቦ የመ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም። የጨረታው አሸናፊዎች ከታወቀ በኋላ ተሸናፊዎቹ ያሲያዙት ገንዘብ ወዲያው ይመለስላቸዋል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና ከታች ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።እንዲሁም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊዎቹም ተለይተው በተገለፀው በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው። ተሸናፊዎቹ ደግሞ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል። አሸናፊዎች በገቡት ውል መሰረት ዕቃዎችን በህብረት ችቦ የመ/ደ/ት/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
መስሪያቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- አዲስ አበባ ከተማ አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ሳሪስ አቦ አዋሽ ቆዳ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0114 431 698
የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት