Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ልደታ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት አንድ:- የተለያየ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት:-ቋሚ እቃዎች
- ሎት ሦስት:- የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት አራት:-የተለያየ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት አምስት -የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥገና
- ሎት ስድስት:-የመስተንግዶ ግዥ
- ሎት ስባት፡- የህትመት ስራዎች
- ሎት ስምንት:- የደንብ ልብስ
- ሎት ዘጠኝ – የመኪና እቃዎች
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ጋር ተዛማጅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ::
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ እና የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ::
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ::
- የአገር ውስጥ የግብዓት አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ካላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለአንድም ሆነ ለሁሉም ሎቶች ብር 15,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C.P.O) ወይም የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: CPO መሠራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:00 ሰዓት ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር በሚወስደው መንገድ ተወልደና ልጆቹ ህንጻ ላይ ልደታ ክ/ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ 6ኛ ፎቅ 602 ቁጥር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ታክሱን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ ማቅረብ አለባችሁ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት 6ኛ ፎቅ 603 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል::
- ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት። ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- የጨረታው አሸናፊ ሲረጋገጥ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ከቋሚ እቃዎች እና ህትመቶች በስተቀር ሌላው ሁሉም ናሙና መምጣት የሚችሉ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችን ማስረከብ አለባቸው ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም ፖስታ ሳይከፈት ውድቅ ይደረጋል::
- የፕሪንተር ቀለም ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት ቀለም አይነት የ 6 ወር የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 0115-50-99-37/0115-57-25-84
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Furniture cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Promotional Items cttx, Electromechanical and Electronics cttx