በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ዕቃና አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 07, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥርA.Ano 1.MTP 100/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች //ቤት

  • የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣
  • አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • የፕሪንተርና የፎቶኮፒ ቀለሞች፤
  • የህትመት ስራዎች
  • የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ ዕቃዎችና የመኪና ተጓዳኝ ዕቃዎች፣
  • ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤
  • ግንባታዎችና የእድሳት ስራዎችን

ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃና አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን ሰርተፊኬት ያላቸው እና ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
  4. የዘመኑን ግብር በመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፤ ለሎት አንድ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ) ለሎት ሁለት ብር 6,000.00 (ስድስት ሺህ) ለሎት ሦስት ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ) ለሎት አራት ብር 6,000.00 (ስድስት ሺህ) ለሎት አምስት ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ) በሲፒኦ (CPO) ወይም በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ የቀድሞው አንበሳ ጫማ ፋብሪካ (ዳርማር) ፊትለፊት ዳሸን ባንክ ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ላይ በሚገኘው የቅ//ቤታችን ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን  ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን  ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
  8.  የጨረታው መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ይከፈታል
  9. ተጫራቾች ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን //ቤቱ ናሙና ላቀረበባቸው ዕቃዎች ናሙናዎቹን በማየት የመጫረቻ ዋጋቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል።
  10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የዕቃውን የስራውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ( አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ወይም የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና በማስያዝ  ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመፈጸም አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በሙሉ //ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ  አለበት።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ አንበሳ ጫማ ፋብሪካ የቀድሞው (ዳርማር) ፊትለፊት ዳሽን ባንክ ሕንፃ

ስልክ 0115-57-71-22 ወይም  09 0115-57-71-34

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች //ቤት