Your cart is currently empty!
በኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በስሩ ላሉ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በስሩ ላሉ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ
- 1. የጽህፈት መሣሪያዎች
- 2. ፈርኒቸሮች
- 3. ኤሌክትሮኒክስ
- 4. የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና እና ሞተርሳይክል ጎማዎች ከነካላመዳሪያቸው
- 5. የሠራኞች የደንብ ልብስ የሚሆን መሳሪያ
- 6. ለህዝብና ለጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች
- 7. የህንጻ መሳሪያ
- 8. ለመንገድ ስራ የሚውሉ ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡–
1. ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2.የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
3. ለጨረታው ማስከበሪያ አስር ሺህ (10,000) ብር የዶረኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የባንክ ሂሳብ ቁጥር 10000289247697 ላይ በማስገባት ስሊፕ ወይም ደረሰኝ ማስያዝ የሚችል።
4. ከ10,000 በላይ ሁለት ፐርሰንት ለመቁረጥ ፈቃደኛ የሆነ።
5. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
6. የታዘዘውን ዕቃዎች እስከ ዶራኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጭኖ ማቅረብ የሚችል
7. ተጫራቾቹ ጨረታውን ካሸነፉ ቀርበው ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆኑና ዕቃዎቹን በራሳቸው ሙሉ ወጪ በታዘዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥረው ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆኑ።
8. ተጫራቾቹ የዕቃው ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በተጨማሪ በጨረታው ዝርዝር ላይ መግለጽ አለባቸው።
9. ተጫራቾቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾቹ ለሚያቀርቧቸው የደንብ ልብሶች እና ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
12. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ አንድ መቶ (100) ብር ከኢሉባቦር ዞን ዶሪኒ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል እና ከዶረኒ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ በመግዛት የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው፣ የሚነበብ መሆን አለበት
13. ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ እና ፈቃድን የሚገልጽ ሰነድ ብቻ ለብቻ በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት ማቅረብ አለባቸው።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ/ ቁጥር፡– 09 12 40 51 03 / 09 13 30 81 31
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉአባቦር
ዞን የዶረኒ ወ/ገ/ጽ/ቤት