በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር)፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና የደምብ ልብስ አቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 03, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በሥሩ ለሚገኙ የመንግስት /ቤቶች የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸር)፤ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፤ የደምብ ልብስ አቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበት የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከወረዳው ገንዘብ /ቤት ግዥ ክፍል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 10,000 (አስር ሺህ) ብር በወረዳው ገንዘብ /ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒ ኦሪጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።

5. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ በመንግስት የግዥ መመሪያ መሠረት ይበረታታሉ።

6. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የስራ ቀን፤ ከቀኑ 0400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 0430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ /ቤት ይከፈታል።

7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላለ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት።

8. አሸናፊው እንደ ታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።

9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ /ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና በራሱ ወጭ መገጣጠም ይኖርባችኋል።

10. /ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: ስልክ ቁጥር፡– 046 443 0204, 0911 767 228 0913 196 281

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ /ቤት