በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር ግዥ ለ1ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ሰነድ በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 04, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር /ቤቶች 1 ዙር ግዥ 1 ጊዜ የወጣ የጨረታ ሰነድ 2018 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፡

  • አላቂ ዕቃዎች/ጽህፈት መሳሪያዎች
  • ኤሌክትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

መመሪያ/ መስፈርት በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን (2017/2018) ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ቫት ከፋይ የሆኑ TIN Number ማቅረብ የሚችሉ።

2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነዱ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለሁ ማለት አይቻልም።

3 ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጓል ቢሞከር ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደ ፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል።

4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቻው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።

6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የግዢ መደብ ብር 5000/አምስ ብር ብቻ በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን በካሽ ከሆነ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት።

7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆኑ የዕቃ ዓይነቶች መሥሪያ ቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጀ ለምሳሌ የኮምፒዩተር ወረቀት፣ እስከሪብቶዎች፣ ኬንት፣ ሶፍት፣ ኡሁ፣ የኮምፒዩተር ቀለም፣ ኦርጅናል የቆዳ ውጤቶች ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሰረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥበቅ እናሳስባለን።

8. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን ጭነው እስከ /ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

9. ተጫራቾቸ ዕቃው የተሰራበትን የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት . መግለጽ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም።

12. /ቤታችን የሚያጫርታቸውን የአንዱ ዋጋ ሲሆን አሸናፈው የሚፈልገውን የዕቃ ብዛት ማዘዝ ይችላል።

13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ ኢድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን ፋከስ ቁጥራቸውን በትከክል ፅፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አላባቸው።

14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጫረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ወይም ለሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

15. /ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ ዕቃው አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዘት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል።

16. የሰነዱ ሸያጭ የሚቆይበት ቀን 27/12/2017 እስከ 21/01/2018 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው 22/01/2018 ከጧቱ 400 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በዛው እለት 430 ሰዓት ላይ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል።

17. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የሰነዱን ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል

18. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውል መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት።

19. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20, አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ወይም በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት።

ለበለጠ መረጃ፡ሞባይል 0942 848 646 / 0911 029 362

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት