Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፤ ቋሚ ዕቃዎች ፈርኒቸር፤ የግንባታ ዕቃዎችን፤ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማ እና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጥገና ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/ 2018
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፦
የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፤ ቋሚ ዕቃዎች ፈርኒቸር፤ የግንባታ ዕቃዎችን፤ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማ እና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጥገና ሥራዎች፤
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተለውን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች በዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. ከብር 100,000 በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥ የሚሣተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዝገቡ መሆን አለባቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፤ ቲን ነምበር እና ፣ የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ አቅራቦት ዘርፍ የጨረታ ማስረከቢያ ብር 6000 (ስድስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅበታል፤ በተጨማሪም አሸናፊው በ 15 ቀን ውስጥ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ቼከ ወይም ሲፒኦ አቅርቦ/ አስይዞ/ ውል መፈረም ግዴታ አለበት፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ፎቶ ኮፒ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከቀርሳ ወረዳ ከገቢዎችና ጉምሩከ በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ) ብር በመከፈል ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ የወረዳው ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 2 እስከ 11፡00 ሰዓት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ገብቶ ሳጥኑ ታሽጎ በእለቱ በ8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ሰነዱ የተሟላ ከሆነ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጎልም፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
6. አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ ማንኛውንም ወጪ ችሎ ቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ እስቶር ( ንብረት ከፍል) ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
7, የጨረታው ሰነድ ከተከፈተ ቀን አንስቶ ለ60 /ስልሣ/ ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
8. ተጫራቾች ተጨማሪ መስፈርቶች ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ ፣ ከብ ማህተም እና ስልክ ቁጥር ሊኖረው ይገባል::
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 113 0478 / 047 113 0011 / በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጅማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ