Your cart is currently empty!
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- ሎት 1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና መገልገያዎች፣
- ሎት 2. የደንብ ልብስ፣
- ሎት 3. አላቂ የጽዳት መገልገያዎች፣
- ሎት 4. ቋሚ እቃ፣
- ሎት 5. የህትመት ውጤቶች፣
- ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
- ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር እና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉና ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ ተስፋ የመጀ/መ/ደ/ት/ቤት የግዢ ክፍል በመቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር የሥራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼከ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለሎት 01. የጨረታ ማስከበሪያ 20000.00 (ሀያ ሺህ ብር)
- ለሎት 02. የጨረታ ማስከበሪያ 20000.00 (ሀያ ሺህ ብር)
- ለሎት 03. የጨረታ ማስከበሪያ 15000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
- ለሎት 04. የጨረታ ማስከበሪያ 15000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
- ለሎት 05 የጨረታ ማስከበሪያ 3000.00 (ሦስት ሺህ ብር)
- ለሎት 06. የጨረታ ማስከበሪያ 4000.00 (አራት ሺህ ብር)
7. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አናቀርብም።
8. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የቅሬታ ጊዜ ጠብቀው የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ለግዢ ፈፃሚው አካል ማስያዝ አለባቸው፤ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው።
9. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ቫትን ጨምሮ በግልፅ መሙላት አለባቸው።
10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. አድራሻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ከቤተል ሆስፒታል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ፤
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-349-9459 ደውለው ይጠይቁ፤
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት