Your cart is currently empty!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጂቡቲ እስከ ቦንጋ የጭነት አገልግሎት መስጠት የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡– ከጂቡቲ እስከ ቦንጋ የጭነት አገልግሎት መስጠት
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
- በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ። ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ጤና ሚኒስቴር ግቢ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 200/ ሁለት መቶ ብር/በመከፈል መውሰድ ይችላሉ። የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ፖስታ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት አዲስ አበባ ጤና ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት አዲስ አበባ ጤና ሚኒስቴር ግቢ ወስጥ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች ያሸነፈበትን አገልግሎት እስከ ቦንጋ ገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግምጃ ቤት ንብረት ከፍል ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና እስከ 6 ወር ድረስ ተቋሙ ተጨማሪ ግዥ ለመፈፀም ፍላጎት ሲያቀርብ ባሸነፈው ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ።
- ተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆስፒታሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 5/አምስት/ ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ።
- ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ጤና ሚኒስቴር ግቢ ወስጥ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0473310316 / 0473311798 ያገኙናል።
በካፋ ዞን የገ/ፃድቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል