አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 05, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግል መለያ ቁጥር አበበች/ጎበና/ የመ/ / / ቤት 01/2017 .

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት 2018 . በጀት አመት የተለያየ በሎት ምድብ የተከፋፈለ እቃዎችን ማለትም፡

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 4 ህትመት
  • ሎት 5 አላቂ የህክምና አቃዎች
  • ሎት 6 አላቂ የትምህርት እቃዎች
  • ሎት 7 አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 8 ዝቅተኛ ቋሚ እቃዎች
  • ሎት 9 ቋሚ ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች
  • ሎት 10 ቋሚ ህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በቅድሚያ ሟሟላት ይኖርባችኋል።

1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ መሆነቸውንና በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅ የግዥ የግልጽ ጨረታን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አበበች ጎበና የመጀመራያ ደረጃ /ቤት ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን 2% ፐርሰንት በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀው ሲፒኦ ከኦርጅናል ማስረጃ ፖስታ ውስጥ ሲፒኦ በማድረግ በመያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶቻቸው ጋር ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ የውል ማስከበሪያ የሚሆን ያሸነፉበትን የገንዘብ መጠን 10% ሲፒኦ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለውል ማስከበሪያ አያገለግልም፡፡

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በአበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሰነዶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡

8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም አቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና መቅረብ አለበት፡፡

9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማህተም በማድረግ በታሸገ ካኪ ፖስታ ሳጥን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 ቀን ቆይቶ በ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ይከፈታል፡

11. ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው አምራችና የአገር ውስጥ ምርት የሚያቀርቡ ከሆኑ ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወደኛ ሰነድ ለመውሰድ ስትመጡ አምራች ስለመሆናችሁና የአገር ውስጥ ምርት መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ ፡፡ነገር ግን አምራችና የአገር ውስጥ ምርት አቅራቢ ካልሆናችሁ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪ መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

12. ማንኛውም ተጫራች ባዘጋጀነው ሰነድ ነው ሞልቶ ማቅረብ የሚቻለው ከዚያ ውጪ ለሚያመጣ ውድቅ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን ሰነዱን ሙሉ ለሙሉ መግዛት ይኖርባችኃል፡፡

13. /ቤቱ የተሻለ የግዢ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻችን፡ዮሐንስ ጸበል አካባቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ በሚያስገባው ወይም በተለምዶ አይሻ መስጊድ አጠገብ  ስልክ ቁጥር– 011 812 6317

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት