Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ስጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ |
የተበዳረው ስም |
የመያዣ ስጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
1 |
አቶ አህመድ አብደሩፍ አልአሚን |
አዋሳ ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ. |
ግንባታቸው የተጠናቀቀ እና በግንባታ ላይ ያለ ለኢንዱስትሪ /ፋብሪካ/ አገልግሎት የሚሆኑ መጋዘኖች /ህንፃዎች/ |
350,000 |
2139 |
ሐዋሳ ከተማ፣ መነሐሪያ ቀበሌ (ሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አከባቢ) |
1,408,715,847.21 |
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
2 |
አቶ ብሩክ አበበ ታፈሰ |
አቶ ብሩክ አበበ ታፈሰ |
ለኢንዱስትሪ /ለፋብሪካ/አገልግሎት የሚውል መጋዘን |
3332.58 |
የቀድሞ 8153/2001 አዲሱ ETH000010253828 የቦታው ልዩ መለያ ቁጥር OR001050126007 |
ምስ/ሸዋ ዞን፣ አዳማ ከተማ፣ ደጋጋ (05) ቀበሌ |
50,453,804.75 |
መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
3 |
አቶ ብሩክ አበበ ታፈሰ |
ወ/ሮ ትዕግስት አለማየሁ አሰፋ |
ለኢንዱስትሪ /ለፋብሪካ/አገልግሎት የሚውል መጋዘን |
2499.75 |
የቀድሞ 735590/97 አዲሱ ETH000010253764 የቦታው ልዩ መለያ ቁጥር OR001050131011 |
ምስ/ሸዋ ዞን፣ አዳማ ከተማ፣ ደጋጋ (05) ቀበሌ |
46,403,850.51 |
መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30 |
9:30-10:00 |
4 |
አቶ መስፍን አግዘው በላይነህ |
ተበዳሪው |
G+6+T፣ የሆነ የንግድ ህንፃ |
328 |
190118/112/2007 |
ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ አሰላ ከተማ፣ ቀበሌ 04 |
42,967,648.26 |
መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
5 |
አቶ መስፍን አግዘው በላይነህ |
አቶ ታደለ ደምሰው አግዘው |
G+4 የሆነ የንግድ ህንፃ |
355 |
18980/71/2006 |
ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ አሰላ ከተማ፣ ቀበሌ 04 |
27,872,978.83 |
መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30 |
9:30-10:00 |