Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል᎓᎓ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
የወጣበት ጊዜ |
1. |
ሚልቶ ጀነራል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ አበበ ሰቦቃ |
መኖሪያ ቤት |
416 |
EMMLM/Sul/344/06 |
በቀድሞ ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ከተማ፣ ቀበሌ ቃሶ ወሰርቢ በአዲሱ አደረጃጀት በሸገር ከተማ፣ መነአቢቹ ክ/ከተማ፣ ቱፋ ሙና ወረዳ |
12,722,968.85 |
ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
2. |
መኖሪያ ቤት |
500 |
Sul/2327/12 |
7,589,729.97 |
ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30 |
9:30-10:00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|||
3. |
መኖሪያ ቤት |
200 |
Sul/2297/12 |
5,771,383.60 |
ጥቅምት 05 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|||
4. |
ይክመኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ ጸጋዬ ባህሩ ገበየሁ |
የኢንዱስትሪ ህንፃ/ መጋዘን/ |
7590.532 |
ደብኢፓ/03/0250/2016 |
በአማራ ብ/ክ/መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ጫጫ ክ/ከተማ |
34,750,446.47 |
ጥቅምት 05 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30 |
9:30-10:00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |