Your cart is currently empty!
አዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወረዳ 11 የሚገኘው የአበቦች ፍሬ የመ/ደ/ት/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወረዳ 11 የሚገኘው የአበቦች ፍሬ የመ/ደ/ት/ቤት 001/2018 ዓ.ም ከዚህ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ላይ በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1፡ የደንብ ልብስ/የልብስ ስፌትን ያካትታል፣
- ሎት2፡ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት3፡ አላቂ የትምህር እቃዎች፣
- ሎት4፡ አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት5: የጥገና ዕቃ ስራዎች እና ዕቃ ግዥ ፣
- ሎት6፡ የቋሚ እቃዎች ግዥ፣
- ሎት7፡–የህትመት ስራዎች
- ሎት8፡ የተለያዩ አገልግሎት ግዥ እና መፅሀፍት ግዥ እና
- ሎት9፡ አላቂ የህክምና እቃዎች ግዥ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራች ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ
2. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin)የተሰጠው/ጣት የሚገልጽ
5. በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብርት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ የአቅራቢነት ዝርዝር (supplier list) መመዝገባቸውን የሚገልጽ ዝርዝር ማቅረብ የሚችሉ።
6. በጨረታ መሳትፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላላፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
7. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከአበቦች ፍሬ የመ/ደ/ት ቤት ሂሳብ ከፍል የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ መደረግ አለበት።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው ማቅረቢያ ላይ የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዋና እና ኮፒውን በመለየት ቲክኒክና ፋይናሽያሉን አንድ ላይ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር)ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአበቦች ፍሬ የመደ ት/ቤት በግዥ/በፋይናንስ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከ2፡30-11፡00 ሰዓት በመምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ከፍል የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መዝጊያ ና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
10. ከጥቃቅን አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች የምትወዳደሩበት እቃ የራሳችሁ ምርት (አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅና በአመረታችሁት እቃ ላይ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን።
11. ት/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ማድረስ አለባቸው። በተጨማሪም እቃዎች ላይ 20% የመጨመር ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
12. ተጫራቾች ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባችኋል። ሁሉም የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንክ በአበቦች ፍሬ የመ ደ/ት/ቤት ስም በCPO በማሰራት ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሎት |
ሎት 1(0.5%) |
ሎት 2 (0.5%) |
ሎት 3 (0.5%) |
ሎት 4 (0.5%) |
ሎት 5 (0.5%) |
ሎት6 (0.5%) |
ሎት 7 (0.5%) |
ሎት 8 (0.5%) |
ሎት 9 (0.5%) |
ብር |
6,000 |
4,000 |
7,500 |
7,500 |
3,250 |
5,500 |
1,250 |
2,750 |
373.4 |
ማሳሰቢያ፡–
- የዕቃዎችን ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
- ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች የጨረታ ውጤት ካሳወቅንበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ሰባት /7/ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
- የግዥ መመሪያውን አንድጋ ተያይዞ መመለስ አለበት።
- የልብስ ስፌት ያሸነፈ ድርጅት ት/ቤቱ ድረስ በመምጣት ለክቶ ሰፍቶ ማስረከብ አለበት።
- አድራሻ ፡– ኮልፌ ልኳንዳ ፈጥኖ ካንፕ መታጠፊያ በቀኝ በኩል 100 ሜትር ገባ ብሎ
- ስልክ ቁጥር፡–011 127 94856/ 011 279 8653/ 011 279 6167 /
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የሚገኘው የአበቦች ፍሬ የመ/ደ/ት/ቤት