የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለሕግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል ለማገዶ እንጨት እና ለምግብ እህል በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለሕግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል ለማገዶ እንጨት እና ለምግብ እህል በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላለ፡

1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

2. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የማገዶ እንጨት እና የምግብ እህል 6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለፁትን ሕጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፤ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረቱ በባንክ ከተረጋገጠ የማገዶ እንጨት CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር እና በባንክ በተረጋገጠ የምግብ እህል CPO 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል

6. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ15ኛው ቀን 400 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከጠዋቱ 430 የእህል ጨረታ ይከፈታል። እንዲሁም የማገዶ እንጨት 830 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

8. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳየት አለበት

9. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ድጋፍ የሥራ ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ማሳሰቢያ /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046-212-8747 መደወል ይችላሉ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *