የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan(Sep 06, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ጨረታ አውጥቶ ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዢያ በባንክ የተረጋገጠ cpo በየሎቱ

ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃዎች

9000 ( ዘጠኝ ሺ ብር)

ሎት 2.የጽዳት፣ የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ ዕቃዎች 

8000 (ስምንት ሺ ብር)

ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች   

15000 (አስራ አምስት ሺ ብር)

ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

15000 ( አስራ አምስት ሺ ብር)

ሎት 5 የጥገና ሥራዎች

5000 (አምስት ሺ ብር)

ሎት 6.የመኪና እና የሞተር ጎማዎች

5000 (አምስት ሺ ብር)

ሎት 7.መስተንግደ ግዥ  

5000 (አምስት ሺ ብር)

ሎት 8.አዳራሽ ዲኮር የወንበር ዲኮር 

5000 (አምስት ሺ ብር)

ሎት 9. የህትመት ስራዎች

5000 (አምስት ሺ ብር)

ሎት 10. የትራንስፖርት /መጓጓዣ) 

2000 (ሁለት ሺ ብር)

ሎት 11. ዘር/አዝዕርት

2000(ሁለት ሺ ብር)

ብቃት ያላቸዉንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳደሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህ መሰረት

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው የተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ፤ቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል በቀድሞው ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በአሁኑ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ o4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 501 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 501 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛ ቀን በ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 501 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  6. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. አሽናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2፣ እና ሎት 7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 3፣ ለሎት 4 እና ለሎት 5 በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት የተሟላ እስፔስፊኬሸን ማዘጋጀት እና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ እንደሆኑ ከተለየ በሆላ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 1o ፐርሰንት ውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ cpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ
  11. አድራሻ አዲስ አበባ በቀድሞው ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በአሁኑ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ከሳር ቤት ወረድ ብሎ ሀረር ከሊኒክ ፊት ለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ የመስሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር 0113834260
  12. በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት