Your cart is currently empty!
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪያ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ፣ የሞተር/ሣይክል መለዋወጫዎች እና ያገለገለ ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪያ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ፣ ምግብ ነክ፣ የሞተር/ሣይክል መለዋወጫዎች እና ያገለገለ ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፡ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሀዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት(1000174515488) የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
3. ማንኛውም ግልፅ ጨረታ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆንየሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 በሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጅው ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ሰነድ እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
5. ማንኛውም ተጫራች የተሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
7. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
8. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
9. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
10. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
11. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046 212 5396
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት