የመነ አብቹ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያቤቶች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ እስቴሽነሪ እቃዎች ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 08, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር መነ አብቹ/001/2018

የመነ አብቹ /ከተማ ገንዘብ /ቤት 2018 በጀት ዓመት በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያቤቶች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ እስቴሽነሪ እቃዎች ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ (አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 230 እስከ 630 እና ከሰዓት 730 እስከ 1130 የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበትን ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO 100,000 (አንድ መቶ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል። ሲፒኦ ማሰራት የሚቻለው በሸገር ከተማ ስር በሚገኙ /ከተሞችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ መሆን አለበት፤፤

7. የጨረታው ዋጋ እቃውን ጨርሰው እስከሚያስገቡ ድረስ ጸንቶ ይቆያል

8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ።

9. ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም፡፡

10. ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ /ቤቱ የማይቀበልና ከውድድር ውጪ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰአት ይታሸግና በእለቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።

12.አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ በደረሰው ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግዢ ፈጻሚ /ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት። ውል ተቀባይ ፈቃደኛ ካልሆነ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታገድ ይደረጋል፡፡

13. የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ CPO የይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ/አገልግሎት/ ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ የውል ማስከበሪያ ሲያሲዙ ቀደም ብለው ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

14. በግዢ ፈጻሚ /ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲያረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል።

15. በጨረታ ለምትወዳደሩበት የእቃ ዝርዝር ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑንና ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60 /ስልሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል።

16. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ /ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስትርት/ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

17.  /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡የመነ አብቹ /ከተማ ገንዘብ /ቤት ሁንዴ ሪዞርት ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 09 13 49 89 73 / 09 34 15 56 17 / 09 11 53 28 72 /

የመነ አብቹ /ከተማ ገንዘብ /ቤት