Your cart is currently empty!
የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 04, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለድርጅቱ አገሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በዚሁ መሠረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ሎት 1 የቧንቧ እና መገጣጠሚያ በተናጠል ግዥ
- ሎት2. የፅህፈት መሳሪያዎችና የፅዳት እቃዎች በተናጠል
- ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በተናጠል
- ሎት4 የደንብ ልብስ በተናጠል
- ሎት5. የኤሌክትሪክ እቃዎች በተናጠል
- ሎት6, ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በተናጠል
- ሎት7 የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች በተናጠል
- ሎት8. ዋተር ኬሚካል ቴስት ታብሌቶች በተናጠል
- ሎት9. የህትመት ስራ ውጤቶችን ብቻ በጠቅላላ ድምር የምናወዳድር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በዚሁ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው::
3. የቫት ተመዝጋቢ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይከ1 – 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሸ/ከ/አስ/ውኃ አገለግሎ ድርጅት በተዘጋጀውየጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከድርጅቱ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% ጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ)ማስያዝ አለባቸው።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸ/ከ/ወኃ አዝ/ሎት ድርጅት ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል። የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
9. ድርጅቱቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉትን ማንኛውንም ንብረት ድርጅታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ድርጅታችን ድረስ በአካል በመገኘት (በስልክ ቁጥር 033 664 0040 / 09 13 51 96 98) በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
11. ማሳሰቢያ፡– የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ሳንፕል ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት