Your cart is currently empty!
የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም ለወረዳው መንግስት መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም ለወረዳው መንግስት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ (በሎት) የተከፋፈሉትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 |
ሎት 2 |
ሎት 3 |
ሎት 4 |
ሎት 5 |
ሎት 6 |
የደንብ ልብስ፣ ፍራሽና አልጋ ልብስ |
የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
የጽዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ ዕቃዎችና መሣሪያዎች |
የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ፣ የመብራት ዕቃዎችና የበር ቁልፎች |
ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ምንጣፎች መጋረጃዎች |
ሞተር ብስክሌቶች |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው እንዲወዳደሩ እናስታውቃለን።
1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቲን(TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ላይ የመንግሥትን ታክስ አካተው (ደምረውበት) ማቅረብ አለባቸው። በጨረታ ሰነድ ላይ የመንግሥት ታክስ መካተቱ (መደመሩ) ካልተገለጸ የቀረበው የጨረታ ሰነድ የመንግሥትን ታክስ እንዳ እንዳልተካተተ ታስቦ ይሰራል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ያለውን እያንዳንዳቸው በብር 100 (መቶ) በማስላት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000036818909 በተከፈው ሂሳብ ገቢ በማድረግና፤ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
6. የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት በቱሉ ቦሎ ከተማ በበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ሠነድ ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን 6፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
8. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
9. ከተገለጸው ሰዓት ውጪ የቀረበው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
10. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) በቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት አምጥቶ ማስረክብ ይኖርበታል።
11.በጨረታ ማስታወቂያና በግዢ ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች የሚለያዩ ከሆነ በሃገር ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች ተቀባይነት ይኖራቸዋል።
12. መ/ቤቱ ከዚህ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
13. አድራሻ፡–በጅማ መሥመር ከአ.አ 80 ኪ.ሜ. ላይ ቱሉቦሎ ከተማ መናኸሪያ አከባቢ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክቁጥር 011 342 0017 / 011 342 1080 / 09 11 94 26 59 / 09 13 30 75 62 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደበብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት /ቱሉቦሎ/