Your cart is currently empty!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ምግብ ፕሮግራም ምገባ ለሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የደስታ ወረቀትና የልብስ ሳሙና የማቅረብና የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EB/EMAS/05/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ምግብ ፕሮግራም ምገባ ለሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የደስታ ወረቀትና የልብስ ሳሙና የማቅረብና የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ ያልቀረበ ተጫራች በውድድሩ ሊሳተፍ አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በቢሮው ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ እስከ ረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582201100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582201666/0583205654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ