Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይገባኝ ኮሚሽን ለራሱ እና በስሩ ላሉ ፑል መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና መጋረጃ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ IT አይቲ ዕቃዎች (ሰርቨር) Server፣ Toner(የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለም) እና ፈርኒቸር/ የእንጨት ስራ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይገባኝ ኮሚሽን ለራሱ እና በስሩ ላሉ ፑል መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሎት1፡– የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2፣ የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና መጋረጃ ሎት3፡– የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ሎት 4፦ IT አይቲ ዕቃዎች (ሰርቨር)Server፣ ሎት 5፡– Toner(የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለም) እና ሎት 6፡– ፈርኒቸር/የእንጨት ስራ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማስራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ /eg-p/ ማያያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር / ተከታታይ የስራ ቀናት ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት፡– የፅህፈት መሳሪያዎች 1000.00/አንድ ሺህ ብር ብቻ/ –የሠራተኛ ደንብ ልብስ እና 1000.00/አንድ ሺህ ብር ብቻ / ሎት 3:- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የእንጨት ስራ 5000.00/አምስት ሺህ ብር ብቻ/፣ ሎት 4 – IT አይቲ ዕቃዎች እና (ሰርቨር) Server 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ሎት 5፡– Toner (የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለም) 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ሎት 6፦ ፈርኒቸር /የእንጨት ስራ 1000.00/ አንድ ሺህ ብር ብቻ
6. በባንክ በተረጋገጠ cpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒክ እና ፋይናንስ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ01/አንድ /ኮፒ ጋር በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል:: ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተወዳዳሪዎች የሚያስገቡትን ደረጃቸውን የጠበቁ እቃዎችን ናሙና በተዘጋጀው ክፍል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 558 2851 በመደወል መጠየቅ ይችላል።
አድራሻ ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን