Your cart is currently empty!
የዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በተቋሙ ለሚገኙ ለተለያዩ ዲፓርትመንት የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ኮምፒውተርና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የብረታ ብረት እቃዎች፣ የግብርና እቃዎች፤ የአኒማል ፕሮዳክሽን ዕቃዎች (Animal Production materials)፣ የአኒማል ሄልዝ (Animal Health) ዕቃዎችና፣ የፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በተቋሙ ለሚገኙ ለተለያዩ ዲፓርትመንት የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ኮምፒውተርና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የብረታ ብረት እቃዎች የግብርና እቃዎች፤ የአኒማል ፕሮዳክሽን ዕቃዎች (Animal Production materials) የአኒማል ሄልዝ (Animal Health) ዕቃዎችና፣ የፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን /2017/የመንግሥት ግብር የከፈሉ እና የገንዘብ ሚኒስቴር እና ክልል ባወጣው እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን የሚያቀርቡ፡፡
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከፍት ሆኖ ስለሚቆይ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ/ በመክፈል በዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ጨረታው በዚሁ በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ልክ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም ተጫራቾች በተጠቀሰው ሰዓት ባይገኙም የጨረታ ሣጥኑን መክፈት አያዳግትም፤ 16ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ የሚመለስ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት መከጡሪ ከተማ ድረስ በማጓጓዝ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ መቻል ይኖርባቸዋል፡፡
6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች የእቃውን ሞዴል ወይም ሳምፕል ማሳየት ግዴታ ነው፡፡
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ እና የመሸጫ ዋጋ በትክክል በታሸገ የጨረታው የመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በአንድ ፖስታ ጋር ተያይዞ/ ኤንቨሎፕ/ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011 134 0894 ደውለው ይጠይቁ።
አድራሻ : ሰሜን ሸዋ ዞን ሙከጡሪ ከተማ በጎጃም መሄጃ አውራ መንገድ ከመነሃሪያ ወረድ ብሎ ከአ.አ 78 KM ርቀት ላይ ይገኛል።
የዋጫሌ ካርል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ