Your cart is currently empty!
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1/2018
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በየሎቱ ተዘርዝረው የተገለፁትን፡–
- ሎት-1 የህትመት ግዢ
- ሎት-2 የፅህፈት እቃዎች ግዢ
- ሎት-3 የፅዳት እቃዎች ግዢ
- ሎት-4 የደንብ ልብስ ግዢ
- ሎት-5 የጎማ እና የመኪና እቃዎች ግዢ
- ሎት-6 ህንፃ ቁሳቁስ እና የጥገና እቃዎች ግዢ
- ሎት-7 ጀነሬተር ሰርቪስ ግዢ
- ሎት-8 የቧንቧ እቃዎች ግዢ
- ሎት-9 የምግብ ግብአቶች ግዢ
- ሎት-10 የኤሌክትሮኒክስ ግዢ
- ሎት-11 የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዢ
- ሎት-12 ፈርኒቸር ግዢ
- ሎት-13 የህክምና እቃ ጥገናና ሰርቪስ ግዥ
- ሎት-14 የህክምና እቃ ግዢ
- ሎት-15 ሰፕላይ ግዢ
- ሎት-16 መድሃኒት ግዢ
- ሎት-17 ሪኤጀንት ግዢ
- ሎት-18 የህክምና እቃዎች ስፔር ፓርት ግዢ
- ሎት-19 ማሽነሪ ግዢ
ከላይ የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው፡–
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ እና ከገቢዎች የታደሰ የመጫረቻ ፈቃድ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሆኖ ሁሉንም የተጠየቁ ማስረጃዎች በግልጽ የሚታይና የሚነበብ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ፣ ዕሁድ የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10 ኛው ቀን 10፡45 ሰአት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ፖስታዎቹ ላይ ከውጪ ሎቶቹን በመፃፍና ማህተም በማድረግ፤ በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦርጂናል የማይመለስ ኮፒውን በመለየት የሚቀርብ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ድረስ ግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሳምፕል፤ ካታሎግ ይቅረብ በተባለው ላይ ያቀርባሉ፤ ስፔስፊኬሽን ያላቸውን በጥንቃቄ በማየት መጫረት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት-1፤ ሎት-2፤ ሎት 3፤ ሎት-4፤ ሎት-5፤ ሎት– 6፤ ሎት-8፤ ሎት-9፤ ሎት-11፤ ላይ ላሉት በእያንዳንዱ ብር 10,000(አስር ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና ሎት -7፤ ሎት-10፤ ሎት-12፤ ሎት-13፤ ሎት-14፤ ሎት– 15፤ ሎት-16፤ሎት– 17፤ሎት-18፤ሎት-19 ላይ ላሉት ለእያንዳንዱ 50,000(ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው ሰነድ መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዢና እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍል በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
10. የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል።
11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባለው የቅሬታ ማቅረቢያ የሚታይበትን ቀን ጨምሮ ከ7 ቀን በኋላ አሸናፊዎች አዋርድ ወስደው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ(CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ በ3 ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች ስፔስፊኬሽኑ እና ሳምፕል የቀረበባቸውን በሳምፕሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. የጨረታ ሳጥኑ ከታሽገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል።
13. የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል።
14. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችለው በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ብቻ ሲሆን በአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማራችሁ የንግድ ስራ መለያ ኮድ በደብዳቤ ላይ በመግለፅ ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል።
15. ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011- 515 -02- 42 በመደወል መረዳት
አድራሻ፡– በቂርቆስ ክ/ከተማ ፍል ውሃ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል