Your cart is currently empty!
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፤ ቁጥር 01
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚያስፈልጉ የምግብ እና መገልገያ እቃዎችን
- ሎት 1. ለምግብ አገልግሎት የሚዉሉ ሩዝ ፣ መኮረኒ ፣ የተዘጋጀ በርበሬ ፣ የተዘጋጀ ሽሮ ፣ቲማቲም ድልህ ወዘተ ፣
- ሎት 2. አትክልት፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ እንቁላል ወዘተ ፣
- ሎት 3. የእርድ በሬ ፣
- ሎት 4. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 5. አላቂ እቃዎች ፣
- ሎት 6. የጽዳት እቃዎች ፣
- ሎት 7. ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 8. ከነጭ ዱቄት የተሰራ ዳቦ ፣
- ሎት 9. የኤሌክትሪክ እቃዎች የህንፃ መሳሪያና የቧንቧ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላችሁ፡፡
- የጨረታ ግዡ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች፣ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ወይም በባንክ በተመሰረተ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1 በመቶ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
- አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
- የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 46 84 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
Bee and Animal Husbandry cttx, cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx Poultry, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Electromechanical and Electronics cttx