Your cart is currently empty!
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቋሚ፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስና ጫማ፣ መጋረጃ፣ የጽዳት እቃዎችና የመኪና ዕቃና ጎማ ከአገር ውስጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01 2018ዓ.ም
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እቃዎችን የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡–
ቋሚ፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስና ጨማ፣ መጋረጃ፣ የጽዳት እቃዎችና የመኪና ዕቃና ጎማ ከአገር ውስጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳታፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል።
1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ መረጃ መቅረብ አለባቸው።
2. የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ግብር ለመሰብሰብ ከተሰጠቸው መ ቤት ወቅታዊ የሆነ መስረጃ መቅረብ አለባቸው።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት
4, የአቅረቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት መቅረብ አለባቸው።
5. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ መቅረብ አለባቸው።
6. ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለጸ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒያቸው ከፊትና ከኋላ ሆኖ የኦርጅናሉን ይዘት በጠበቀ መልኩ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000(አምስት ሺህ) ብር በደቡብ ምዕረብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም አሰርተው ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረገጋጠ (CPO) ከሚያቀርባቸው ሠነዶች ጋር አያይዞ መቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ እንደላ ሆኖ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ አስቀድሞ ከባንክ ማረጋገጫ የሚወሰድ ይሆናል።
8. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 7 ላይ የተጠቀሰውን (CPO) ካላስያዘ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
9. ለጥቃቂን ኢንተርፒረይዞች ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋንታ ከአደረጁ መ/ቤት የተጻፈ ወቅታዊ የሆነ የዋስትና ደብዳቤ መቅረብ ይኖርበታል።
10. ተጫረቾች ለጫረተው የተዘገጀውን ዶክመንት ወይም የጫረታው ሰነድ ከደቡብ ምዕረብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሊሶ ከተማ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአከል በመቅረብ የዕቃውን ምድብ አይነት lot/ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከወጠው ቀን ጀምሮ ከ30/12/2017 እስከ 16/01/2018 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ።
11. ጨረታውን ለማሰናከል የሚሞክር ተጫራች ከጫረታው ውጪ ሆኖ ወደፊት በሚደረገው በማንኛውም ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ አየር ላይ የሚቆይ ይሆናል።
13. የጨረተው ሰነድ በ 19/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀለት የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚህ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
14. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ከለይ ከ1-14 ተረቁጥር የተጠቀሰውን ሳያሟላ የሚቀረብ ተጫረች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
ለተጨማሪ መብራሪያ
አድራሻ፡–የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወሊሶ ከተማ
ስልክ ቁጥር፡– 0113411484/0113411396
Email:- mmosk@oromiyaa.gov.et
ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።