የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 07, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ 2018 በጀት 1 ዙር ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል፡

  • ሎት ı – አላቂ የቢሮ ዕቃ፣
  • ሎት 2 – ህትመት፣
  • ሎት 3 – የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 4 – የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 5 – የቢሮ ቋሚ አላቂ መገልገያዎች፣
  • ሎት 6 – ቋሚ እቃዎች፣
  • ሎት 7 – ለፕላንት፣ ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት፣
  • ሎት 8 – ለህንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና፣
  • ሎት9 – ለግብርና፣ ለደንና ለባህር ግብዓቶች፣
  • ሎት 10 – ስፌት፣
  • ሎት 11 – ለተሽከርካሪ እና ሌሎች መጓጓዣዎች፣
  • ሎት 12 – መድሃኒት፣

1. ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን /2017/ ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች መሆናቸውን የሚገልጽና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከመ/ቤቱ ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

  • ለሎት 1 – ብር 5,000.00
  • ለሎት 2 – 5,000.00
  • ለሎት 3 – 5,000.00
  • ለሎት 4 _ 5,000.00
  • ለሎት 5 – 5,000.00
  • ለሎት 6 – 10,000
  • ለሎት 7 – 10,000
  • ለሎት 8 – 10,000.00
  • ለሎት 9 – 5,000.00
  • ለሎት 10 – 5,000
  • ለሎት 11– 5,000.00
  • ለሎት 12 – 7,000.00

4. ተጫራቾች የሚጫረቱት የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦሪጅናል ሰነድ ላይ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ላይ ኮፒ በማለት ለየብቻቸው በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁለቱም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 411 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ናሙና የሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገለጻል።

6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 400 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ 4 ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ነው።

7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. ግዥ ፈጻሚው /ቤት ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የግዥ መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

9. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

አድራሻ፡

  • ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል ያሬድ ቤተ ክርስቲያ ፊት ለፊት
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡ 011-4-70-08-44 መጠየቅ ይችላሉ

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ