Your cart is currently empty!
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሲንከር፣ ጅፕሰም እና ሲሚንቶ ) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/58/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሲንከር፣ ጅፕሰም እና ሲሚንቶ) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የንግድ ምዝገባና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2017/18 ዓ/ም) የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖረሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በገዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ 011 442 0216 /
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ