Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት የመኪናና የሞተር ሳይክል ጥገና እና እድሳት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል
Melekite Dire(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመኪናና የሞተር ሳይክልጥገናእና እድሳት ጨረታ ማስታወቂያ
የጨ / መ/ ቁ/ ፋ/ኢ 001/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት
- የመኪናና የሞተር ሳይክል ጥገና እና እድሳት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡–
- በዘርፉ የተሠማሩና ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው አና በመንግስት የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቶች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የተሸከርካሪ አድሳትናጥገናዎች ሁሉንም የጥገናና የእድሳት አይነቶች በራሳቸው ጋራዥ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማለትም የሞተር ፓርት ፤ የኤሌክትሪክ ፓርት እና የጠቅላላ ቦዲ ጥገና እድሳት ሁሉንም የእድሳትና ጥገና አይነቶች ያካተተ ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ በድሬ ጋዜጣ በማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምሰት) ተከታታይ የስራ ቀናት ድርስ የጨረታ ሠነዱን ብር 300ብር በመክፈል ከግዥ/ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 212 ቀርበው በመውሰድ አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይችላሉ፣
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በዳይሬክቶሬቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ለመኪና ጥገናና እድሳት ብር 10,000(አስር ሽህ) ለሞተርሳይክል እድሳትና ጥገና ብር 5,000(አምሰት ሽህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፤በጥሬ ገንዘብ ፤እንዲሁም በሲፒኦ(CPO) ከጨረታ ሠነዱጋርማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡–
ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬተ
የስልክ ቁጥር 0915732312 ወይንም
0928118000
ድሬ ዳዋ