Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ እንዲቻል የመንግስት ፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት እና ልዩ ልዩ ደረሰኞች ህትመት በድሬ ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Melekite Dire(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂየ የጨ/መ/ቁ ግዥን /512/የመግ/ጨ 01/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ እንዲቻል የመንግስት ፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት እና ልዩ ልዩ ደረሰኞች ህትመት በድሬ ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚሁ መሠረት ፡–
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን በፋይናንስ ኮኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 109 ቀርበው ብር 200.00 /ሁለት መቶ / መግዞት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሰነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀወ የጨረታ ሣጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሣውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ፋይናንስ ግልጽነትና ተጠይቂነት ሎት አንድ ብር 30.000.00 / ሰላሣ ሺ ብር / እና የተለያዩ የደረሰኝ ህትመቶች ብር 40.000.00 / አርባ ሺ / የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ሲያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፡–
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 215
የስልክ ቁጥር 0915 75 57 68 /0915 00 10 86
ድሬዳዋ