Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አውቶሞቢል ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216 92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ቅርንጫፍ |
የንብረቱ ባለቤት |
የንብረቱ ስም እና ዓይነት |
የሞተር እና የሻንሲ ቁጥር |
የሰሌዳ ቁጥር
|
የተመረተበት ዓመት |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) |
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
1 |
ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን ኃ.የተ.የግ.ማኅበር |
የመስቀል ገበያ |
አቶ ወዴሳ ያቺሲ ቡሉልታ |
አውቶሞቢል |
SQRF4J16AVNJ08593 እና LVUDB21B5Pr024951
|
አአ-02-C43315 |
2022 |
3,633,120.00 |
22/01/2018 ዓ.ም 3:00 – 4:00 ጠዋት |
2 |
ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን ኃ.የተ.የግ.ማኅበር |
የመስቀል ገበያ |
ተበዳሪው |
አውቶሞቢል |
0175574PSA10TMA3HN05 እና VF3MRHNSUNS070481
|
አአ-03-B58204 |
2022 |
4,541,400.00 |
22/01/2018 ዓ.ም 4:00 – 5:00 ጠዋት |
3 |
ወ/ሮ ውዳሴ አበበ ቸኮል |
መንበረ ፓትርያሪክ
|
ቴዎድሮስ አበበ ቸኮል |
አውቶሞቢል |
FEAJ11HRA2*696746ል እና SJNFEAJ11UL2399086 |
AA-02-B52539 |
2018 |
2,673,000.00 |
22/01/2018 ዓ.ም 5:00 – 6:00 ጠዋት |
በመሆኑም፡–
1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል።
2. ሐራጁ የሚከናወነው አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በሚገኘዉ የህግ ክፍሉ የስብሰባ አዳራሽ (ቢሮ ቁጥር 4203) ነዉ።
3. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
4. ለጨረታ ከቀረቡ የመኖሪያ ቤቶች ዉጪ የሆኑ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል። ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሒደት ለመንግሥት የሚከፈል ማንኛውም ክፍያ ገዥ ይከፍላል።
5. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በመገኘት (ባንኩ በሚያመቻቸዉ ፕሮግራም መሰረት) መጎብኘት ይችላሉ።
6. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
7. የባንኩን የብድር ቅደመ ሁኔታ ለሚያሟሉ ተጫራቾች ባንኩ ብድር ሊፈቅድ ይችላል።
8. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።