Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት አንድ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የሊፋን መኪና የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 88/3 መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዳግም ተመዝግቦ በመዝገብ ቁጥር 1417 ህጋዊ ሰውነት ያለው ሀገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅታችን አንድ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ከ2ኛው ቀን በኋላ ንብረቶቹ በሚገኙበት ከኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት በመግኘት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታው በጸደቀ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ሲያስገቡ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ ተሸናፊዎች ጨረታው በጸደቀ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በአድራሻችን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት /15/ ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው። በአስራ አምስተኛው /15/ቀን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱን ድርጅቱ ይወርሳል።
- ተጫራቾች የድርጅቱን የተሽከርካሪ ዝርዝርና የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 1000/ አንድ ሺህ ብር/ እንዲሁም ከተሽከርካሪ ውጪ ያሉ ንብረቶችን ዝርዝር የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስራ አምስተኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 5፡15 ተጫራቾችና ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ወጪ በገዢ የሚሸፈን ይሆናል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251911111714 በስራ ሰዓት ብቻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- ወደ ቄራ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ናሳ ካፌ ገባ ብሎ 80 ሜትር ኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ህንፃ ውስጥ ነው።
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት