Your cart is currently empty!
የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ዘምዘም አብዱልቃድር እና የፍ/ባለዕዳ አቶ አህመድ ኪሞ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 187949 በ10/03/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/196374 በ30/5/2016 ዓ/ም በ2/03/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት፡–
1ኛ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3–B21192 አ/አ D4D ቶዮታ የህዝብ ተሸከርካሪ ዶልፊን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,700,000 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ብር) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3-B21543 አ/አ ቶዮታ ሃይሉከስ ድርብ ተግባር (የ2021 ምርት) የሐራጅ መነሻ ዋጋ 9,500,000 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም 4፡30 ሰዓት በሐራጅ ይሸጣል።
3ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3 A 08331 ኢት ሲኖ ትራክ የደረቅ ጭነት መኪና (የ2021 ምርት) የሐራጅ መነሻ ዋጋ 8,500,000 (ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት በሐራጅ ይሸጣል።
4ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠቁ ኮድ3 84182 አ/አ አይሱዙ አልሙኒየም ኮንቲነር ያለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ 2,5000,00 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል ሆኖ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም 8፡00 በሐራጅ ይሸጣል።
5ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3-32412 ኢት ተሳቢ (220 ኩንታል የሚጭን) የሐራጅ መነሻ ዋጋ 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም 8፡30 ሰዓት በሐራጅ ይሸጣል።
6ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3-96830 አ/አ IVECO (0m) የደረቅ ጭነት መኪና የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም 9፡00 ሰዓት በሐራጅ ይሸጣል።
7ኛ ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠቁ ኮድ3-96828 አእ IVECO (om) የደረቅ ጭነት (ከ10 ኩንታል የበለጠ) ተሸከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1000.000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓም 9፡30 ሰዓት በሐራጅ ይሸጣል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግባት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ : ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ/አፈ/ዳ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በጨረታ አሸናፊ የሆነው በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፌ/ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት